Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika

Nomor Halaman:close

external-link copy
97 : 17

وَمَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُمۡ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِهِۦۖ وَنَحۡشُرُهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمۡ عُمۡيٗا وَبُكۡمٗا وَصُمّٗاۖ مَّأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ كُلَّمَا خَبَتۡ زِدۡنَٰهُمۡ سَعِيرٗا

97. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀና ማለት እርሱው ነው:: እርሱ ያጠመማቸውን ግን ከቅጣቱ የሚያድናቸው ማንም ወዳጅ አታገኝላቸዉም:: የትንሳኤ ቀንም እውር፤ ዲዳና፤ ደንቆሮ አድርገን በፊቶቻቸው እየተጎተቱ እንሰበስባቸዋለን:: መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት:: ሀይሏ በደከመ ጊዜም ግለትን እንጨምርላቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
98 : 17

ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُم بِأَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَقَالُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا وَرُفَٰتًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ خَلۡقٗا جَدِيدًا

98. ይህ ቅጣት የሚጠብቃቸው ቅጣታቸው ነው:: ምክንያቱም በመልዕክተኞቻችን ክደው «የበሰበሰ አጥንት ከሆንና (ወደ አቧራነት) ከተቀየርን በኋላ እንደ አዲስ እንቀሰቀሳለን?» በማለታቸውም ነው። info
التفاسير:

external-link copy
99 : 17

۞ أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ قَادِرٌ عَلَىٰٓ أَن يَخۡلُقَ مِثۡلَهُمۡ وَجَعَلَ لَهُمۡ أَجَلٗا لَّا رَيۡبَ فِيهِ فَأَبَى ٱلظَّٰلِمُونَ إِلَّا كُفُورٗا

99. ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አላህ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ መሆኑን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበትንም ጊዜ ለሞትም ለትንሳኤም ለእነርሱ የወሰነ መሆኑን አላወቁምን? በደለኞችም ከክህደት በስተቀር እምቢ አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
100 : 17

قُل لَّوۡ أَنتُمۡ تَمۡلِكُونَ خَزَآئِنَ رَحۡمَةِ رَبِّيٓ إِذٗا لَّأَمۡسَكۡتُمۡ خَشۡيَةَ ٱلۡإِنفَاقِۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ قَتُورٗا

100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የጌታዬን የችሮታ መካዚኖች ብትይዙ ኖሮ ያን ጊዜ በማውጣታችሁ ማለቋን በመፍራት በጨበጣችሁ ነበር:: ሰው በጣም ንፉግ ነውና።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
101 : 17

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ تِسۡعَ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۖ فَسۡـَٔلۡ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ إِذۡ جَآءَهُمۡ فَقَالَ لَهُۥ فِرۡعَوۡنُ إِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰمُوسَىٰ مَسۡحُورٗا

101. ለሙሳ ግልጽ የሆኑን ዘጠኝ ተዓምራት በእርግጥ ሰጠነው:: በመጣቸዉም ጊዜ የኢስራኢልን ልጆች ከፈርዖን እንዲለቀቁ ጠይቅ አልነው:: ፈርዖንም፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ የተደገመብህ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
102 : 17

قَالَ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَآ أَنزَلَ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ بَصَآئِرَ وَإِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰفِرۡعَوۡنُ مَثۡبُورٗا

102. ሙሳም፡- «እነዚህን ተዓምራት መግሰጫዎች ሲሆኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ አውቀሀል:: እኔም ፈርዖን ሆይ! የምትጠፋ መሆንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
103 : 17

فَأَرَادَ أَن يَسۡتَفِزَّهُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ فَأَغۡرَقۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ جَمِيعٗا

103. ከምድርም ሊያባርራቸው አሰበ:: እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ሁሉንም አሰመጥናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
104 : 17

وَقُلۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِۦ لِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱسۡكُنُواْ ٱلۡأَرۡضَ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ ٱلۡأٓخِرَةِ جِئۡنَا بِكُمۡ لَفِيفٗا

104. ከእርሱም በኋላ ለኢስራኢል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት:: የኋለኛይቱም ሰዓት ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትሆኑ እናመጣችኋለን።» አልናቸው። info
التفاسير: