Terjemahan makna Alquran Alkarim - Terjemahan Berbahasa Amhar - Akademi Afrika

አል ኢስራዕ

external-link copy
1 : 17

سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِيٓ أَسۡرَىٰ بِعَبۡدِهِۦ لَيۡلٗا مِّنَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ إِلَى ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡأَقۡصَا ٱلَّذِي بَٰرَكۡنَا حَوۡلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنۡ ءَايَٰتِنَآۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ

1. ጥራት ለዚያ ባሪያውን (ሙሐመድን) ከተከበረው የሐረም መስጊድ ወደ እዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ሩቁ (አል አቅሷ) መስጊድ በሌሊት ለወሰደው አምላክ ለአላህ ይሁን:: ይህን ያደረግን ተዓምራታችንን ልናሳየው ነው:: እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚዉና ተመልካቹ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 17

وَءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَجَعَلۡنَٰهُ هُدٗى لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُواْ مِن دُونِي وَكِيلٗا

2. ለሙሳም (ተውራት የተባለውን) መጽሐፍ ሰጠነውና ለኢስራኢል ልጆች መሪ አደረግነው:: ከእኔ ሌላ ወኪል (መጠጊያ) አድርጋችሁ ማንንም አታድርጉ“ስንልም አዘዝናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 17

ذُرِّيَّةَ مَنۡ حَمَلۡنَا مَعَ نُوحٍۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَبۡدٗا شَكُورٗا

3. «ከኑህ ጋር (በመርከቧ ላይ) የጫንናቸው (አማኝ )ዝርዮች ሆይ! (አላህን ተገዙ)፤ ኑህ በእርግጥ አምላኩን በብዛት አመስጋኝ ባሪያ ነበርና» አልናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 17

وَقَضَيۡنَآ إِلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ لَتُفۡسِدُنَّ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَّتَيۡنِ وَلَتَعۡلُنَّ عُلُوّٗا كَبِيرٗا

4. ለኢስራኢል ልጆችም፡ “በምድር ላይ ሁለት ጊዜ ጥፋት ትፈጽማላችሁ:: አለቅጥም አምባገነን ትሆናላችሁ::” ስንል በመጽሐፉ ውስጥ ገለጽን:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 17

فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ أُولَىٰهُمَا بَعَثۡنَا عَلَيۡكُمۡ عِبَادٗا لَّنَآ أُوْلِي بَأۡسٖ شَدِيدٖ فَجَاسُواْ خِلَٰلَ ٱلدِّيَارِۚ وَكَانَ وَعۡدٗا مَّفۡعُولٗا

5. ከሁለቱ የመጀመሪያው ጥፋት መፈጸሚያ ወቅቱ በደረሰ ጊዜ የበረታ ኃይል ያላቸውን ባሮቻችንን በእናነተ ላይ ላክንባችሁ:: እነርሱም ቤቶችን ሁሉ በረበሩ:: ይህ መፈጸሙ የማይቀር ውሳኔ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 17

ثُمَّ رَدَدۡنَا لَكُمُ ٱلۡكَرَّةَ عَلَيۡهِمۡ وَأَمۡدَدۡنَٰكُم بِأَمۡوَٰلٖ وَبَنِينَ وَجَعَلۡنَٰكُمۡ أَكۡثَرَ نَفِيرًا

6. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ የድል አድራጊነትን እድል ሰጠናችሁ:: ገንዘብንና ወንዶች ልጆችንም ለገስናችሁ:: በሰው ኃይልም ብዙ አደረግናችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 17

إِنۡ أَحۡسَنتُمۡ أَحۡسَنتُمۡ لِأَنفُسِكُمۡۖ وَإِنۡ أَسَأۡتُمۡ فَلَهَاۚ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ ٱلۡأٓخِرَةِ لِيَسُـُٔواْ وُجُوهَكُمۡ وَلِيَدۡخُلُواْ ٱلۡمَسۡجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَلِيُتَبِّرُواْ مَا عَلَوۡاْ تَتۡبِيرًا

7. መልካምን ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ:: መጥፎንም ብትሠሩ በነፍሶቻችሁ ላይ ነው:: የኋለኛይቱ ጥፋት ቀጠሮ በደረሰ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፤ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡቡት ሊገቡ፤ ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋለን:: info
التفاسير: