કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
30 : 41

إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُواْ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسۡتَقَٰمُواْ تَتَنَزَّلُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُواْ وَلَا تَحۡزَنُواْ وَأَبۡشِرُواْ بِٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ

30. እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም ቀጥ ያሉ። እንዲህ እያሉ መላዕክቱ በነርሱ ላይ ይወርዳሉ: «አትፍሩ አትዘኑ:: በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላቸሁ:: በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 41

نَحۡنُ أَوۡلِيَآؤُكُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۖ وَلَكُمۡ فِيهَا مَا تَشۡتَهِيٓ أَنفُسُكُمۡ وَلَكُمۡ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ

31. «እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አላችሁ:: ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምታዙት ሁሉ አለላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 41

نُزُلٗا مِّنۡ غَفُورٖ رَّحِيمٖ

32. «መሀሪና አዛኝ ከሆነው አላህ መስተንግዶ ሲሆን» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 41

وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ

33. ወደ አላህ ከጠራንና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለው ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? info
التفاسير:

external-link copy
34 : 41

وَلَا تَسۡتَوِي ٱلۡحَسَنَةُ وَلَا ٱلسَّيِّئَةُۚ ٱدۡفَعۡ بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ فَإِذَا ٱلَّذِي بَيۡنَكَ وَبَيۡنَهُۥ عَدَٰوَةٞ كَأَنَّهُۥ وَلِيٌّ حَمِيمٞ

34. መልካሚቱና ክፉይቱም ጸባይ አይስተካሉም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ መጥፎይቱን ገፍትር፤ ያን ጊዜ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ ወዳጅ ዘመድ ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 41

وَمَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ٱلَّذِينَ صَبَرُواْ وَمَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ذُو حَظٍّ عَظِيمٖ

35. ይህችንም ጸባይ እነዚያን የታገሱት እንጂ ሌላው አያገኛትም:: የትልቅም እድል ባለቤት እንጂ ማንም አያገኛትም:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 41

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ نَزۡغٞ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

36. ከሰይጣን ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጸባይ ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 41

وَمِنۡ ءَايَٰتِهِ ٱلَّيۡلُ وَٱلنَّهَارُ وَٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُۚ لَا تَسۡجُدُواْ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ ٱلَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ

37. ሌሊትና ቀንም ጸሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው። ለጸሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ:: እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ (ለሌላ አትስገዱ):: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 41

فَإِنِ ٱسۡتَكۡبَرُواْ فَٱلَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ يُسَبِّحُونَ لَهُۥ بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَهُمۡ لَا يَسۡـَٔمُونَ۩

38. ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ:: እነርሱም አይሰለቹም:: {1} info

{1} እዚህ የቲላዋ ሱጁድ ይደረጋል።

التفاسير: