કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

ፉሲለት

external-link copy
1 : 41

حمٓ

1. ሓ፤ ሚይም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 41

تَنزِيلٞ مِّنَ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

2. ይህ ቁርኣን እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ከሆነው ጌታ ከአላህ የተወረደ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 41

كِتَٰبٞ فُصِّلَتۡ ءَايَٰتُهُۥ قُرۡءَانًا عَرَبِيّٗا لِّقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ

3. አናቅጾቹ የተብራሩ የሆነ መጽሐፍ ነው:: ዐረበኛ ቁርኣን ሲሆን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 41

بَشِيرٗا وَنَذِيرٗا فَأَعۡرَضَ أَكۡثَرُهُمۡ فَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ

4. አብሳሪና አስፈራሪ ሲሆን ተወረደ። አብዛኞቻቸዉም ተውት:: እነርሱም አይሰሙም:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 41

وَقَالُواْ قُلُوبُنَا فِيٓ أَكِنَّةٖ مِّمَّا تَدۡعُونَآ إِلَيۡهِ وَفِيٓ ءَاذَانِنَا وَقۡرٞ وَمِنۢ بَيۡنِنَا وَبَيۡنِكَ حِجَابٞ فَٱعۡمَلۡ إِنَّنَا عَٰمِلُونَ

5. አሉም፡- «ልቦቻችን ከዚያ ወደርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው:: በጆሮቻችንም ላይ ድንቁርና አለ:: በእኛና በአንተ መካከል ግርዶሽ አለ:: በሃይማኖትህ ስራ እኛም ሰሪዎች ነንና::» info
التفاسير:

external-link copy
6 : 41

قُلۡ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يُوحَىٰٓ إِلَيَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ فَٱسۡتَقِيمُوٓاْ إِلَيۡهِ وَٱسۡتَغۡفِرُوهُۗ وَوَيۡلٞ لِّلۡمُشۡرِكِينَ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እንዲህ በላቸው «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ቀጥ በሉ:: ምህረትንም ለምኑት በማለት ወደ እኔ ይወርድልኛል እንጂ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ።» ለአጋሪዎችም ወዮላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 41

ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ كَٰفِرُونَ

7. ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡ እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲያን ለሆኑት (ወዮላቸው):: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 41

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ أَجۡرٌ غَيۡرُ مَمۡنُونٖ

8. እነዚያ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ የማይቋረጥ ምንዳ አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 41

۞ قُلۡ أَئِنَّكُمۡ لَتَكۡفُرُونَ بِٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَرۡضَ فِي يَوۡمَيۡنِ وَتَجۡعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادٗاۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !) «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባላንጣዎች ታደርጋላችሁን? ያ (ይህንን የሰራው) የዓለማቱ ጌታ ነው።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 41

وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِيَ مِن فَوۡقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقۡوَٰتَهَا فِيٓ أَرۡبَعَةِ أَيَّامٖ سَوَآءٗ لِّلسَّآئِلِينَ

10. በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ:: በእርሷም በረከትን አደረገ:: በውስጧም ምግቦችዋን (ካለፉት ሁለት ቀኖች ጋር) በአራት ቀናት ውስጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆን ወሰነ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 41

ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِيَ دُخَانٞ فَقَالَ لَهَا وَلِلۡأَرۡضِ ٱئۡتِيَا طَوۡعًا أَوۡ كَرۡهٗا قَالَتَآ أَتَيۡنَا طَآئِعِينَ

11. ከዚያም እርሷ ጭስ ሆና ሳለች ወደ ሰማይ አሰበ:: ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ሆነ ጠልታችሁ ኑ» አላቸው:: «ታዛዦች ሆነን መጣን» አሉ:: info
التفاسير: