કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
36 : 27

فَلَمَّا جَآءَ سُلَيۡمَٰنَ قَالَ أَتُمِدُّونَنِ بِمَالٖ فَمَآ ءَاتَىٰنِۦَ ٱللَّهُ خَيۡرٞ مِّمَّآ ءَاتَىٰكُمۚ بَلۡ أَنتُم بِهَدِيَّتِكُمۡ تَفۡرَحُونَ

36. መልዕክተኛው ሱለይማንን በመጣውም ጊዜ አለ፡- «በገንዘብ ትረዱኛላችሁን? አላህም የሰጠን ከሰጣችሁ የበለጠ ነው:: ይልቁንም እናንተ በገጸበረከታችሁ ትደሰታላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 27

ٱرۡجِعۡ إِلَيۡهِمۡ فَلَنَأۡتِيَنَّهُم بِجُنُودٖ لَّا قِبَلَ لَهُم بِهَا وَلَنُخۡرِجَنَّهُم مِّنۡهَآ أَذِلَّةٗ وَهُمۡ صَٰغِرُونَ

37. «ወደ እነርሱ ተመለስ:: ለእነርሱም በእርሷ ችሎታ በሌላቸው ሰራዊት እንመጣባቸዋለን:: ከእርሷም እነርሱ የተዋረዱ ሆነው በእርግጥ እናወጣቸዋለን።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 27

قَالَ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ أَيُّكُمۡ يَأۡتِينِي بِعَرۡشِهَا قَبۡلَ أَن يَأۡتُونِي مُسۡلِمِينَ

38. «እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ሙስሊሞች ሆነው ወደ እኔ ሳይመጡ በፊት ዙፋኗን የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው?» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 27

قَالَ عِفۡرِيتٞ مِّنَ ٱلۡجِنِّ أَنَا۠ ءَاتِيكَ بِهِۦ قَبۡلَ أَن تَقُومَ مِن مَّقَامِكَۖ وَإِنِّي عَلَيۡهِ لَقَوِيٌّ أَمِينٞ

39. ከጋኔን ሃይለኛው «ከችሎትህ ከመነሳትህ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ:: እኔም በእርሱ ላይ ብርቱ ታማኝ ነኝ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 27

قَالَ ٱلَّذِي عِندَهُۥ عِلۡمٞ مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِ أَنَا۠ ءَاتِيكَ بِهِۦ قَبۡلَ أَن يَرۡتَدَّ إِلَيۡكَ طَرۡفُكَۚ فَلَمَّا رَءَاهُ مُسۡتَقِرًّا عِندَهُۥ قَالَ هَٰذَا مِن فَضۡلِ رَبِّي لِيَبۡلُوَنِيٓ ءَأَشۡكُرُ أَمۡ أَكۡفُرُۖ وَمَن شَكَرَ فَإِنَّمَا يَشۡكُرُ لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ رَبِّي غَنِيّٞ كَرِيمٞ

40. ያ እርሱ ዘንድ ከመጽሐፉ ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው «የተገለጸው ዓይንህ ወደ አንተ ከመመለሱ በፊት እኔ እርሱን አመጣልሃለሁ።» አለ:: እንደዚሁም አደረገ:: እርሱ ዘንድ ረግቶ ባየዉም ጊዜ «ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው። የማመሰግን ወይም የምክድ መሆኔን ሊሞክረኝ ቸረልኝ:: አላህን ያመሰገነ ሁሉ የሚያመሰግነው ለራሱ ነው:: አላህን የካደም ሰው ሁሉ ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ፤ ቸር ነው።» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 27

قَالَ نَكِّرُواْ لَهَا عَرۡشَهَا نَنظُرۡ أَتَهۡتَدِيٓ أَمۡ تَكُونُ مِنَ ٱلَّذِينَ لَا يَهۡتَدُونَ

41. «ዙፋኗን ለእርሷ አሳስቱ ታውቀው እንደሆነ ወይም ከእነዚያ ከማያውቁት ትሆን እንደሆነ እናያለን።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 27

فَلَمَّا جَآءَتۡ قِيلَ أَهَٰكَذَا عَرۡشُكِۖ قَالَتۡ كَأَنَّهُۥ هُوَۚ وَأُوتِينَا ٱلۡعِلۡمَ مِن قَبۡلِهَا وَكُنَّا مُسۡلِمِينَ

42. በመጣችም ጊዜ፡- «ዙፋንሽ እንደዚህ ነውን?» ተባለች «እርሱ ልክ እርሱን ነው የመሰለኝ።» አለች። ሱለይማንም አለ: «ከእርሷ በፊትም እውቀትን ተሰጠን:: ሙስሊሞችም ነበርን። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 27

وَصَدَّهَا مَا كَانَت تَّعۡبُدُ مِن دُونِ ٱللَّهِۖ إِنَّهَا كَانَتۡ مِن قَوۡمٖ كَٰفِرِينَ

43. «ከአላህ ሌላ ትገዛው የነበረችውንም ከለከላት:: እርሷ ከከሓዲያን ሕዝቦች ነበረችና።» info
التفاسير:

external-link copy
44 : 27

قِيلَ لَهَا ٱدۡخُلِي ٱلصَّرۡحَۖ فَلَمَّا رَأَتۡهُ حَسِبَتۡهُ لُجَّةٗ وَكَشَفَتۡ عَن سَاقَيۡهَاۚ قَالَ إِنَّهُۥ صَرۡحٞ مُّمَرَّدٞ مِّن قَوَارِيرَۗ قَالَتۡ رَبِّ إِنِّي ظَلَمۡتُ نَفۡسِي وَأَسۡلَمۡتُ مَعَ سُلَيۡمَٰنَ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

44. «ሕንጻውን ግቢ።» ተባለች:: ባየችዉም ጊዜ ባህር ነው ብላ ጠረጠረችው:: ከባቶቿም ገለጠች:: «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ህንጻ ነው።» አሏት:: «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩኝ።» አለች። info
التفاسير: