કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
23 : 27

إِنِّي وَجَدتُّ ٱمۡرَأَةٗ تَمۡلِكُهُمۡ وَأُوتِيَتۡ مِن كُلِّ شَيۡءٖ وَلَهَا عَرۡشٌ عَظِيمٞ

23. «እኔ የምትገዛቸው የሆነችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ:: ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አላት። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 27

وَجَدتُّهَا وَقَوۡمَهَا يَسۡجُدُونَ لِلشَّمۡسِ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَصَدَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّبِيلِ فَهُمۡ لَا يَهۡتَدُونَ

24. «እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለጸሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው። ሰይጣንም ለእነርሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል። ከእውነተኛዉም መንገድ አግዷቸዋል:: ስለዚህ እነርሱ ወደ እውነት አይመሩም። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 27

أَلَّاۤ يَسۡجُدُواْۤ لِلَّهِ ٱلَّذِي يُخۡرِجُ ٱلۡخَبۡءَ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَيَعۡلَمُ مَا تُخۡفُونَ وَمَا تُعۡلِنُونَ

25. «ለዚያም በሰማያትና በምድር ዉስጥ የተደበቀውን ለሚያወጣው የምትሸሽጉትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ ሰይጣን አግዷቸዋል። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 27

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ۩

26. «አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» (አለ) {1} info

{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱ ትላወህ) ይደረጋል።

التفاسير:

external-link copy
27 : 27

۞ قَالَ سَنَنظُرُ أَصَدَقۡتَ أَمۡ كُنتَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

27. ሱለይማንም አለ፡- «እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደሆንክ ወደ ፊት እናያለን። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 27

ٱذۡهَب بِّكِتَٰبِي هَٰذَا فَأَلۡقِهۡ إِلَيۡهِمۡ ثُمَّ تَوَلَّ عَنۡهُمۡ فَٱنظُرۡ مَاذَا يَرۡجِعُونَ

28. «ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ሂድ:: ወደ እነርሱም ጣለው ከዚያ ከእነርሱ ዘወር በልና ምን እንደሚመልሱም ተመልከት።» info
التفاسير:

external-link copy
29 : 27

قَالَتۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ إِنِّيٓ أُلۡقِيَ إِلَيَّ كِتَٰبٞ كَرِيمٌ

29. እርሷም በደረሳት ጊዜ አለች፡- «እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሑፍ ወደ እኔ ተጣለ። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 27

إِنَّهُۥ مِن سُلَيۡمَٰنَ وَإِنَّهُۥ بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

30. «እርሱ ከሱለይማን ነው። እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 27

أَلَّا تَعۡلُواْ عَلَيَّ وَأۡتُونِي مُسۡلِمِينَ

31. «‹በእኔ ላይ አትኩሩ:: ታዛዦችም ሆናችሁ ወደ እኔ ኑ› የሚል ነው።» info
التفاسير:

external-link copy
32 : 27

قَالَتۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ أَفۡتُونِي فِيٓ أَمۡرِي مَا كُنتُ قَاطِعَةً أَمۡرًا حَتَّىٰ تَشۡهَدُونِ

32. «እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ የሚበጀውን ንገሩኝ እስከምትነግሩኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 27

قَالُواْ نَحۡنُ أُوْلُواْ قُوَّةٖ وَأُوْلُواْ بَأۡسٖ شَدِيدٖ وَٱلۡأَمۡرُ إِلَيۡكِ فَٱنظُرِي مَاذَا تَأۡمُرِينَ

33. «እኛ የሃይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን:: ግን ትዕዛዙ ከወደ አንቺ ብቻ ነው። ምን እንደምታዝዢንም አስተውይ» አሏት:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 27

قَالَتۡ إِنَّ ٱلۡمُلُوكَ إِذَا دَخَلُواْ قَرۡيَةً أَفۡسَدُوهَا وَجَعَلُوٓاْ أَعِزَّةَ أَهۡلِهَآ أَذِلَّةٗۚ وَكَذَٰلِكَ يَفۡعَلُونَ

34. እርሷም አለች፡- «ንጉሶች ከተማን በሃይል በገቡባት ጊዜ ያበላሿታል የተከበሩ ሰዎቿንም ወራዶች ያደርጋሉ:: ልክ እንደዚሁ ነው የሚያደርጉት። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 27

وَإِنِّي مُرۡسِلَةٌ إِلَيۡهِم بِهَدِيَّةٖ فَنَاظِرَةُۢ بِمَ يَرۡجِعُ ٱلۡمُرۡسَلُونَ

35. «እኔም ወደ እነርሱ ገጸበረከትን የምልክና መልዕክተኞቹ በምን እንደሚመልሱ የምጠባበቅ ነኝ።» info
التفاسير: