કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
13 : 11

أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ فَأۡتُواْ بِعَشۡرِ سُوَرٖ مِّثۡلِهِۦ مُفۡتَرَيَٰتٖ وَٱدۡعُواْ مَنِ ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «ቁርኣንን ቀጣጠፈው» ይላሉን? «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን አስር የተቀጣጠፉ ምዕራፎች እስቲ አምጡ:: ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ረዳት ጥሩ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 11

فَإِلَّمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَكُمۡ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَآ أُنزِلَ بِعِلۡمِ ٱللَّهِ وَأَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَهَلۡ أَنتُم مُّسۡلِمُونَ

14. ለእናንተ ምላሽ ካልሰጧችሁ «(ጣዖት አምላኪያን ሆይ!) የተወረደው በአላህ እውቀት ብቻ መሆኑንና ከእርሱ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም እወቁ:: እናም አትሰልሙምን?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 11

مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيۡهِمۡ أَعۡمَٰلَهُمۡ فِيهَا وَهُمۡ فِيهَا لَا يُبۡخَسُونَ

15. ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሁሉ ሥራዎቻቸውን ምንዳዋን በእርሷ ውስጥ ወደ እነርሱ እንሞላላቸዋለን:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 11

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَيۡسَ لَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِلَّا ٱلنَّارُۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُواْ فِيهَا وَبَٰطِلٞ مَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

16. እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከእሳት በስተቀር የሌላቸው ናቸው:: የሰሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ:: በቅርቢቱ ዓለም ይሰሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 11

أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّهِۦ وَيَتۡلُوهُ شَاهِدٞ مِّنۡهُ وَمِن قَبۡلِهِۦ كِتَٰبُ مُوسَىٰٓ إِمَامٗا وَرَحۡمَةًۚ أُوْلَٰٓئِكَ يُؤۡمِنُونَ بِهِۦۚ وَمَن يَكۡفُرۡ بِهِۦ مِنَ ٱلۡأَحۡزَابِ فَٱلنَّارُ مَوۡعِدُهُۥۚ فَلَا تَكُ فِي مِرۡيَةٖ مِّنۡهُۚ إِنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤۡمِنُونَ

17. ከጌታው ዘንድ አስረጅ የደረሰውንና ከእርሱም የሆነ መስካሪ የሚከተለው ከቁርኣን በፊትም ለሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲሆን የመሰከረለት (ሰውና) የቅርቢቱን ህይወት እንደሚሻው (ሰው) ነውን? እነዚያ በእርሱ (ቁርኣን) ያምናሉ:: ከአህዛቦቹ በእርሱ የሚክድ ሰው ሁሉ መመለሻው እሳት ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: እሱ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እውነት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 11

وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ يُعۡرَضُونَ عَلَىٰ رَبِّهِمۡ وَيَقُولُ ٱلۡأَشۡهَٰدُ هَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ كَذَبُواْ عَلَىٰ رَبِّهِمۡۚ أَلَا لَعۡنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ

18. በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀረባሉ:: መስካሪዎቹም «እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹት ናቸው።» ይላሉ:: «አስተዉሉ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ብቻ ይሁን።» ይባላል። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 11

ٱلَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَيَبۡغُونَهَا عِوَجٗا وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ كَٰفِرُونَ

19. እነርሱም እነዚያ ከአላህ መንገድ ሰዎችን የሚከለክሉ የአላህን መንገድ መጥመሟንም የሚሹት ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን ናቸው። info
التفاسير: