કુરઆન મજીદના શબ્દોનું ભાષાંતર - એમ્હારિક ભાષામાં અનુવાદ - આફ્રિકન એકેડમી

પેજ નંબર:close

external-link copy
82 : 11

فَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا جَعَلۡنَا عَٰلِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهَا حِجَارَةٗ مِّن سِجِّيلٖ مَّنضُودٖ

82. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ከተማይቱን ላይዋን ከታችዋ አድርገን ገለበጥናት:: ተከታታይም የሆነን የሸክላ ድንጋይ በእርሷ ላይ አዘነብንባት:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 11

مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَۖ وَمَا هِيَ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ بِبَعِيدٖ

83. ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)። እርሷም (መንደሯ) ከበደለኞቹ ህዝቦች ሩቅ አይደለችም:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 11

۞ وَإِلَىٰ مَدۡيَنَ أَخَاهُمۡ شُعَيۡبٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ وَلَا تَنقُصُواْ ٱلۡمِكۡيَالَ وَٱلۡمِيزَانَۖ إِنِّيٓ أَرَىٰكُم بِخَيۡرٖ وَإِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٖ مُّحِيطٖ

84. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን:: አላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: ስፍርንና ሚዛንን አታጉሉ:: እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ:: እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
85 : 11

وَيَٰقَوۡمِ أَوۡفُواْ ٱلۡمِكۡيَالَ وَٱلۡمِيزَانَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ

85. «ህዝቦቼ ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: ሰዎችን መብቶቻቸውን አታጓድሉባቸው:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ። info
التفاسير:

external-link copy
86 : 11

بَقِيَّتُ ٱللَّهِ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيۡكُم بِحَفِيظٖ

86. «አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ትክክለኛ አማኞች እንደ ሆናችሁ አላህ በሰጣችሁ ውደዱ። እኔም መካሪ እንጂ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።» info
التفاسير:

external-link copy
87 : 11

قَالُواْ يَٰشُعَيۡبُ أَصَلَوٰتُكَ تَأۡمُرُكَ أَن نَّتۡرُكَ مَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَآ أَوۡ أَن نَّفۡعَلَ فِيٓ أَمۡوَٰلِنَا مَا نَشَٰٓؤُاْۖ إِنَّكَ لَأَنتَ ٱلۡحَلِيمُ ٱلرَّشِيدُ

87. «ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣኦታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን እንድንተው ታዝሃለችን? አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑው አንተ ነህና።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
88 : 11

قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَرَزَقَنِي مِنۡهُ رِزۡقًا حَسَنٗاۚ وَمَآ أُرِيدُ أَنۡ أُخَالِفَكُمۡ إِلَىٰ مَآ أَنۡهَىٰكُمۡ عَنۡهُۚ إِنۡ أُرِيدُ إِلَّا ٱلۡإِصۡلَٰحَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُۚ وَمَا تَوۡفِيقِيٓ إِلَّا بِٱللَّهِۚ عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُ وَإِلَيۡهِ أُنِيبُ

88. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ እስቲ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን? የከለከልኳችሁንም ነገር በመፈጸም ልለያችሁ አልሻም:: በተቻለኝ ያህል ማበጀትን እንጂ አልሻም:: ለደግ ሥራ መታደሌ በአላህ ፈቃድ ብቻ እንጂ በሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ወደ እርሱም እመለሳለሁ። info
التفاسير: