Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique

Numéro de la page:close

external-link copy
4 : 57

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يَعۡلَمُ مَا يَلِجُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا يَخۡرُجُ مِنۡهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعۡرُجُ فِيهَاۖ وَهُوَ مَعَكُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ

4. እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ብቻ የፈጠረ ነው:: ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። ወደ ምድር የሚገባውንና ከእርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: ከሰማይ የሚወረደውንና ወደ እርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: እርሱ የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከናንተው ጋር ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 57

لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ

5. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 57

يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِۚ وَهُوَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

6. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ሁሉ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 57

ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَأَنفِقُواْ مِمَّا جَعَلَكُم مُّسۡتَخۡلَفِينَ فِيهِۖ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَأَنفَقُواْ لَهُمۡ أَجۡرٞ كَبِيرٞ

7. (ሰዎች ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኛው እመኑ:: አላህ በእርሱ ላይ ተተካኪዎች ካደረጋችሁ ገንዘብ ዉስጥም ለግሱ:: እነዚያ ከእናንተ መካከል በአላህ ያመኑትና የለገሱት ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 57

وَمَا لَكُمۡ لَا تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلرَّسُولُ يَدۡعُوكُمۡ لِتُؤۡمِنُواْ بِرَبِّكُمۡ وَقَدۡ أَخَذَ مِيثَٰقَكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

8. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ቃልኪዳናችሁን የያዘባችሁ ሲሆን መልዕክተኛውም በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑበት ምን ምክኒያት አላችሁ? እናንተ በትክክል የምታምኑ ከሆናችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
9 : 57

هُوَ ٱلَّذِي يُنَزِّلُ عَلَىٰ عَبۡدِهِۦٓ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ لِّيُخۡرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ بِكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ

9. እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሀን ሊያወጣችሁ ግልፆች የሆኑን አናቅጽ በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው:: አላህ ለእናንተ በእርግጥ ሩህሩህ አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 57

وَمَا لَكُمۡ أَلَّا تُنفِقُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَا يَسۡتَوِي مِنكُم مَّنۡ أَنفَقَ مِن قَبۡلِ ٱلۡفَتۡحِ وَقَٰتَلَۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَعۡظَمُ دَرَجَةٗ مِّنَ ٱلَّذِينَ أَنفَقُواْ مِنۢ بَعۡدُ وَقَٰتَلُواْۚ وَكُلّٗا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

10. የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ሲሆን በአላህ መንገድ የማትለግሱበት ምን ምክንያት አላችሁ? ከናንተ መካከል ከመካ መከፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው ከተከፈተ በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ሰው ጋር አይስተከከልም:: ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸውና:: ሁሉንም አላህ የመልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 57

مَّن ذَا ٱلَّذِي يُقۡرِضُ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥ وَلَهُۥٓ أَجۡرٞ كَرِيمٞ

11. ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ አላህ ምንዳውን የሚያነባብርለት ሰው ማን ነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አለው:: info
التفاسير: