Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique

አዝ ዙኽሩፍ

external-link copy
1 : 43

حمٓ

1. ሓ፤ሚም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 43

وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ

2. ገላጭ በሆነው መጽሐፍ እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 43

إِنَّا جَعَلۡنَٰهُ قُرۡءَٰنًا عَرَبِيّٗا لَّعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ

3. እኛ ታውቁ ዘንድ ቁርኣንን በዐረብኛ ቋንቋ አደረግነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 43

وَإِنَّهُۥ فِيٓ أُمِّ ٱلۡكِتَٰبِ لَدَيۡنَا لَعَلِيٌّ حَكِيمٌ

4. እርሱም እኛ ዘንድ በመጽሐፎቹ እናት (መሰረት) ውስጥ ያለ፤ እርግጥ ከፍተኛ ማዕረግ ያለውና በጥበብ የተሞላ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 43

أَفَنَضۡرِبُ عَنكُمُ ٱلذِّكۡرَ صَفۡحًا أَن كُنتُمۡ قَوۡمٗا مُّسۡرِفِينَ

5. ድንበር አላፊዎች ህዝቦች በመሆናችሁ ምክኒያት ቁርኣኑን ከማውረድ ከናንተ ማገድን እናግዳለንን? (አናግድም):: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 43

وَكَمۡ أَرۡسَلۡنَا مِن نَّبِيّٖ فِي ٱلۡأَوَّلِينَ

6. በፊተኞቹም ህዝቦች ውስጥ ከነብያት መካከል ብዙን ልከናል:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 43

وَمَا يَأۡتِيهِم مِّن نَّبِيٍّ إِلَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

7. ከነብይም አንድንም የሚመጣላቸው አልነበረም በእርሱ ይቀልዱበት (ያፌዙበት) የነበሩ ቢሆን እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 43

فَأَهۡلَكۡنَآ أَشَدَّ مِنۡهُم بَطۡشٗا وَمَضَىٰ مَثَلُ ٱلۡأَوَّلِينَ

8. ከእነርሱም በሀይል ይበልጥ የበረቱትን አጥፍተናል:: የፊተኞቹም አጠፋፍ ምሳሌ አልፏል። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 43

وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ خَلَقَهُنَّ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡعَلِيمُ

9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ማን ፈጠራቸው?» ብለህ ብትጠይቃቸው «ያ ሁሉን አሸናፊዉና ሁሉን አዋቂው ጌታ ነው የፈጠራቸው» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 43

ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ مَهۡدٗا وَجَعَلَ لَكُمۡ فِيهَا سُبُلٗا لَّعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ

10. አላህ ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በእርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው:: info
التفاسير: