Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique

Numéro de la page:close

external-link copy
30 : 3

يَوۡمَ تَجِدُ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا عَمِلَتۡ مِنۡ خَيۡرٖ مُّحۡضَرٗا وَمَا عَمِلَتۡ مِن سُوٓءٖ تَوَدُّ لَوۡ أَنَّ بَيۡنَهَا وَبَيۡنَهُۥٓ أَمَدَۢا بَعِيدٗاۗ وَيُحَذِّرُكُمُ ٱللَّهُ نَفۡسَهُۥۗ وَٱللَّهُ رَءُوفُۢ بِٱلۡعِبَادِ

30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሰራችውን የቀረበ ሆኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ):: ከመጥፎም የሰራችው በእርሷና በኃጢአቱ መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች:: አላህ እራሱን ያስጠነቅቃችኋል:: አላህ ለባሮቹ ሩህሩህ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 3

قُلۡ إِن كُنتُمۡ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِي يُحۡبِبۡكُمُ ٱللَّهُ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡ ذُنُوبَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ:: አላህም ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 3

قُلۡ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَۖ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡكَٰفِرِينَ

32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ። ብሸሹም አላህ ከሓዲያንን አይወድም» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 3

۞ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصۡطَفَىٰٓ ءَادَمَ وَنُوحٗا وَءَالَ إِبۡرَٰهِيمَ وَءَالَ عِمۡرَٰنَ عَلَى ٱلۡعَٰلَمِينَ

33. አላህ (ነብዩ) አደምን፣(ነብዩ) ኑህን፣(የነብዩ) ኢብራሂምን ቤተሰብ እና የዒምራንን ቤተሰብ ከአለማት አበለጣቸው (መረጣቸው)። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 3

ذُرِّيَّةَۢ بَعۡضُهَا مِنۢ بَعۡضٖۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

34. እኒህን ቤተሰቦች ከፊሉ ከከፊሉ የሆነ ዝርያ አድርጎ መረጣቸው። አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 3

إِذۡ قَالَتِ ٱمۡرَأَتُ عِمۡرَٰنَ رَبِّ إِنِّي نَذَرۡتُ لَكَ مَا فِي بَطۡنِي مُحَرَّرٗا فَتَقَبَّلۡ مِنِّيٓۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

35. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዒምራን ባለቤት (ሀና) «ጌታዬ ሆይ! በሆዴ ውስጥ ያለውን ጽንስ ከሥራ ነፃ የተደረገ ሲሆን ላንተ አገልግሎት ይውል ዘንድ ተሳልኩ:: እናም ተቀበለኝ:: አንተ ሰሚና አዋቂ ነህና።» ባለች ጊዜ የሆነውን አስታውሱ በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 3

فَلَمَّا وَضَعَتۡهَا قَالَتۡ رَبِّ إِنِّي وَضَعۡتُهَآ أُنثَىٰ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا وَضَعَتۡ وَلَيۡسَ ٱلذَّكَرُ كَٱلۡأُنثَىٰۖ وَإِنِّي سَمَّيۡتُهَا مَرۡيَمَ وَإِنِّيٓ أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ

36. በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! ሴት ሆና ወለድኳት።» አለች። አላህ የወለደችውን ምንነት አዋቂ ነው:: የተመኘችው ወንድ እንደ ወለደቻት ሴት የሚሆን አልነበረም:: «መርየምም ብዬ ስም አወጣሁላት:: እኔም እርሷንና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን ተንኮል ባንተ እጠብቃቸዋለሁ።» አለች። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 3

فَتَقَبَّلَهَا رَبُّهَا بِقَبُولٍ حَسَنٖ وَأَنۢبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنٗا وَكَفَّلَهَا زَكَرِيَّاۖ كُلَّمَا دَخَلَ عَلَيۡهَا زَكَرِيَّا ٱلۡمِحۡرَابَ وَجَدَ عِندَهَا رِزۡقٗاۖ قَالَ يَٰمَرۡيَمُ أَنَّىٰ لَكِ هَٰذَاۖ قَالَتۡ هُوَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِۖ إِنَّ ٱللَّهَ يَرۡزُقُ مَن يَشَآءُ بِغَيۡرِ حِسَابٍ

37. ጌታዋም በመልካም አቀባበል ተቀበላት:: በመልካም አስተዳደግም አፋፋት:: ከዚያም ዘከርያ አሳደጋት:: ዘከርያም ወደ ምኩራቧ በሷ ላይ በገባ ቁጥርም እርሷ ዘንድ ሲሳይን አገኘ:: «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው የሚመጣልሽ?» አላት። «እርሱ የሚመጣልኝ ከአላህ ዘንድ ነው:: አላህ እኮ ለሚሻው ሁሉ ሲሳዩን ያለ ሂሳብ ይሰጣል።» አለችው። info
التفاسير: