Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique

Numéro de la page:close

external-link copy
5 : 18

مَّا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٖ وَلَا لِأٓبَآئِهِمۡۚ كَبُرَتۡ كَلِمَةٗ تَخۡرُجُ مِنۡ أَفۡوَٰهِهِمۡۚ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبٗا

5.ለእነርሱም ሆነ ለአባቶቻቸው ስለ አላህ ልጅ መኖር ምንም እውቀት የላቸዉም:: ከአፎቻቸው የሚወጣው ቃል ምን አከበደው! ውሸትን እንጂ ሌላን አይናገሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 18

فَلَعَلَّكَ بَٰخِعٞ نَّفۡسَكَ عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِمۡ إِن لَّمۡ يُؤۡمِنُواْ بِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِ أَسَفًا

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዚህም ንግግር በቁርኣን ካላመኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን ይፈራልሀል:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 18

إِنَّا جَعَلۡنَا مَا عَلَى ٱلۡأَرۡضِ زِينَةٗ لَّهَا لِنَبۡلُوَهُمۡ أَيُّهُمۡ أَحۡسَنُ عَمَلٗا

7.እኛ ማንኛቸው ሥራው ያማረ መሆኑን ልንፈትናቸው በምድር ላይ ያለን ሁሉ የእርሷ ጌጥ አደረግን:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 18

وَإِنَّا لَجَٰعِلُونَ مَا عَلَيۡهَا صَعِيدٗا جُرُزًا

8. እኛ በእርሷ ላይ ያለውን ሁሉ በመጨረሻ ቡቃያ የሌለበት ምልጥ አፈር አድራጊዎች ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 18

أَمۡ حَسِبۡتَ أَنَّ أَصۡحَٰبَ ٱلۡكَهۡفِ وَٱلرَّقِيمِ كَانُواْ مِنۡ ءَايَٰتِنَا عَجَبًا

9-(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዋሻውና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራታችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን? info
التفاسير:

external-link copy
10 : 18

إِذۡ أَوَى ٱلۡفِتۡيَةُ إِلَى ٱلۡكَهۡفِ فَقَالُواْ رَبَّنَآ ءَاتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحۡمَةٗ وَهَيِّئۡ لَنَا مِنۡ أَمۡرِنَا رَشَدٗا

10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወጣቶቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና: «ጌታችን ሆይ! ካንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን:: ለእኛም ከነገራችን ቅንን ነገር አዘጋጅልን።» ባሉ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውስ።) info
التفاسير:

external-link copy
11 : 18

فَضَرَبۡنَا عَلَىٰٓ ءَاذَانِهِمۡ فِي ٱلۡكَهۡفِ سِنِينَ عَدَدٗا

11. በዋሻዉም ውስጥ የተቆጠሩን ዓመታት በጆሮዎቻቸው ላይ መታንባቸው (አስተኛናቸው):: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 18

ثُمَّ بَعَثۡنَٰهُمۡ لِنَعۡلَمَ أَيُّ ٱلۡحِزۡبَيۡنِ أَحۡصَىٰ لِمَا لَبِثُوٓاْ أَمَدٗا

12.ከዚያም ከሁለቱ ክፍሎች ለቆዩት ጊዜ ልክ ያረጋገጠው ማንኛው መሆኑን ልናውቅ ከተኙበት አስነሳናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 18

نَّحۡنُ نَقُصُّ عَلَيۡكَ نَبَأَهُم بِٱلۡحَقِّۚ إِنَّهُمۡ فِتۡيَةٌ ءَامَنُواْ بِرَبِّهِمۡ وَزِدۡنَٰهُمۡ هُدٗى

13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወሬያቸውን ባንተ ላይ በእውነት እንተርክልሃለን:: እነርሱ በጌታቸው በትክክል ያመኑ ወጣቶች ናቸው:: ወደ ቀናው መንገድ መመራትንም ጨመርንላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 18

وَرَبَطۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ إِذۡ قَامُواْ فَقَالُواْ رَبُّنَا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَن نَّدۡعُوَاْ مِن دُونِهِۦٓ إِلَٰهٗاۖ لَّقَدۡ قُلۡنَآ إِذٗا شَطَطًا

14. በንጉሳቸው ፊት በቆሙና እንዲህም ባሉ ጊዜ ልቦቻቸውን በእምነት አጠነከርን: «ጌታችን የሰማያትና የምድር ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክን አንገዛም:: ከእሱ ሌላን ብናመልክማ ወሰን ያለፈን ንግግር በእርግጥ ተናገርን። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 18

هَٰٓؤُلَآءِ قَوۡمُنَا ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةٗۖ لَّوۡلَا يَأۡتُونَ عَلَيۡهِم بِسُلۡطَٰنِۭ بَيِّنٖۖ فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا

15. «እነዚህ ህዝቦቻችን ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙ:: እውነተኞች ከሆኑ በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን ለምን አያመጡም? በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማን ነው?» አሉ። info
التفاسير: