Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Académie d'Afrique

Numéro de la page:close

external-link copy
63 : 11

قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي مِنۡهُ رَحۡمَةٗ فَمَن يَنصُرُنِي مِنَ ٱللَّهِ إِنۡ عَصَيۡتُهُۥۖ فَمَا تَزِيدُونَنِي غَيۡرَ تَخۡسِيرٖ

63. ሷሊህም አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማነው? ከማጥፋትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 11

وَيَٰقَوۡمِ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمۡ ءَايَةٗۖ فَذَرُوهَا تَأۡكُلۡ فِيٓ أَرۡضِ ٱللَّهِۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابٞ قَرِيبٞ

64. «ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ለእናንተ ታዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት:: ተዋትም በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ:: በክፉም አትንኳት። ቅርብ የሆነ ቅጣት ያገኛችኋልና።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 11

فَعَقَرُوهَا فَقَالَ تَمَتَّعُواْ فِي دَارِكُمۡ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٖۖ ذَٰلِكَ وَعۡدٌ غَيۡرُ مَكۡذُوبٖ

65. ወግተው ገደሏትም ሷሊህም «በሀገራችሁም ሶስትን ቀናት ብቻ ተጠቀሙ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው።» አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 11

فَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا صَٰلِحٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَمِنۡ خِزۡيِ يَوۡمِئِذٍۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡعَزِيزُ

66. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳንን:: ከዚያም ቀን ውርደት አዳንናቸው:: ጌታህ ብርቱውና ሁሉን አሸናፊው ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 11

وَأَخَذَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلصَّيۡحَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دِيَٰرِهِمۡ جَٰثِمِينَ

67. እነዚያን የበደሉትንም ከባድ ጩኸት ያዛቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ የተንበረከኩ ሙት በድን ሆነው አደሩ(አነጉ):: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 11

كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَآۗ أَلَآ إِنَّ ثَمُودَاْ كَفَرُواْ رَبَّهُمۡۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّثَمُودَ

68. በእርሷ ውስጥ እንዳልኖሩ ሆኑ:: አስተውሉ! ሠሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ:: አስተውሉ! ለሠሙዶች ከአላህ እዝነት መራቅ ተገባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
69 : 11

وَلَقَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُنَآ إِبۡرَٰهِيمَ بِٱلۡبُشۡرَىٰ قَالُواْ سَلَٰمٗاۖ قَالَ سَلَٰمٞۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَآءَ بِعِجۡلٍ حَنِيذٖ

69. መልዕክተኞቻችንም ወደ ኢብራሂም በልጅ መውለድ ብስራት መጡለትና ሰላም አሉት:: እሱም ሰላም አላቸው:: ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ:: info
التفاسير:

external-link copy
70 : 11

فَلَمَّا رَءَآ أَيۡدِيَهُمۡ لَا تَصِلُ إِلَيۡهِ نَكِرَهُمۡ وَأَوۡجَسَ مِنۡهُمۡ خِيفَةٗۚ قَالُواْ لَا تَخَفۡ إِنَّآ أُرۡسِلۡنَآ إِلَىٰ قَوۡمِ لُوطٖ

70. እጆቻቸዉም ወደ ምግቡ የማይደርሱ መሆናቸውን ባየ ጊዜ ተግባራቸው እንግዳ ሆነበት:: ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው:: «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ህዝቦች ተልከናልና።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
71 : 11

وَٱمۡرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٞ فَضَحِكَتۡ فَبَشَّرۡنَٰهَا بِإِسۡحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسۡحَٰقَ يَعۡقُوبَ

71. ሚስቱም ቁማ ነበርና ሳቀች:: እናም በኢስሓቅ አበሰርናት:: ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በየዕቁብ አበሰርናት:: info
التفاسير: