Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Muhammad Sâdiq

Numéro de la page:close

external-link copy
36 : 6

۞ إِنَّمَا يَسۡتَجِيبُ ٱلَّذِينَ يَسۡمَعُونَۘ وَٱلۡمَوۡتَىٰ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ ثُمَّ إِلَيۡهِ يُرۡجَعُونَ

ጥሪህን የሚቀበሉት እነዚያ የሚሰሙት ብቻ ናቸው፡፡ ሙታንንም አላህ ይቀሰቅሳቸዋል፡፡ ከዚያም ወደርሱ ብቻ ይመለሳሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 6

وَقَالُواْ لَوۡلَا نُزِّلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ قَادِرٌ عَلَىٰٓ أَن يُنَزِّلَ ءَايَةٗ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

«ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም» አሉ፡፡ «አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 6

وَمَا مِن دَآبَّةٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا طَٰٓئِرٖ يَطِيرُ بِجَنَاحَيۡهِ إِلَّآ أُمَمٌ أَمۡثَالُكُمۚ مَّا فَرَّطۡنَا فِي ٱلۡكِتَٰبِ مِن شَيۡءٖۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ يُحۡشَرُونَ

ከተንቀሳቃሽም በምድር (የሚኼድ)፤ በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም ከዚያም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 6

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا صُمّٞ وَبُكۡمٞ فِي ٱلظُّلُمَٰتِۗ مَن يَشَإِ ٱللَّهُ يُضۡلِلۡهُ وَمَن يَشَأۡ يَجۡعَلۡهُ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

እነዚያም በአንቀጾቻችን ያስዋሹ ደንቆሮች ድዳዎችም በጨለማዎች ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ አላህ (ማጥመሙን) የሚሻውን ሰው ያጠመዋል፡፡ (መምራቱን) የሚሻውንም ሰው በቀጥተኛ መንገድ ላይ ያደርገዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 6

قُلۡ أَرَءَيۡتَكُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُ ٱللَّهِ أَوۡ أَتَتۡكُمُ ٱلسَّاعَةُ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَدۡعُونَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

የአላህ ቅጣት ቢመጣባችሁ ወይም ሰዓቲቱ (ትንሣኤ) ብትመጣባችሁ ከአላህ ሌላን ትጠራላችሁን እውነተኞች እንደ ኾናችሁ ንገሩኝ በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 6

بَلۡ إِيَّاهُ تَدۡعُونَ فَيَكۡشِفُ مَا تَدۡعُونَ إِلَيۡهِ إِن شَآءَ وَتَنسَوۡنَ مَا تُشۡرِكُونَ

አይደለም እርሱን ብቻ ትጠራላችሁ፡፡ ቢሻም ወደርሱ የምትጠሩበትን ነገር ያስወግዳል፡፡ የምታጋሩትንም ነገር ትተዋላችሁ (በላቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 6

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰٓ أُمَمٖ مِّن قَبۡلِكَ فَأَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡبَأۡسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ لَعَلَّهُمۡ يَتَضَرَّعُونَ

ከበፊትህም ወደ ነበሩት ሕዝቦች (መልክተኞችን) በእርግጥ ላክን፡፡ እንዲዋደቁም በድህነትና በበሽታ ያዝናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 6

فَلَوۡلَآ إِذۡ جَآءَهُم بَأۡسُنَا تَضَرَّعُواْ وَلَٰكِن قَسَتۡ قُلُوبُهُمۡ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይዋደቁም ኖሯልን ግን ልቦቻቸው ደረቁ፡፡ ይሠሩት የነበሩትንም ነገር ሰይጣን ለነሱ አሳመረላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 6

فَلَمَّا نَسُواْ مَا ذُكِّرُواْ بِهِۦ فَتَحۡنَا عَلَيۡهِمۡ أَبۡوَٰبَ كُلِّ شَيۡءٍ حَتَّىٰٓ إِذَا فَرِحُواْ بِمَآ أُوتُوٓاْ أَخَذۡنَٰهُم بَغۡتَةٗ فَإِذَا هُم مُّبۡلِسُونَ

በርሱም ይገሰጹበት የነበረውን ነገር በተው ጊዜ በእነሱ ላይ የነገርን ሁሉ ደጃፎች ከፈትን (አስመቸናቸው)፡፡ በተሰጡትም ነገር በተደሰቱ ጊዜ በድንገት ያዝናቸው፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ተስፋ ቆራጮች ኾኑ፡፡ info
التفاسير: