Traduction des sens du Noble Coran - La traduction amharique - Muhammad Sâdiq

Numéro de la page:close

external-link copy
75 : 23

۞ وَلَوۡ رَحِمۡنَٰهُمۡ وَكَشَفۡنَا مَا بِهِم مِّن ضُرّٖ لَّلَجُّواْ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ

ባዘንንላቸውና ከጉዳትም በእነርሱ ያለውን ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ኾነው ይዘወትሩ ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
76 : 23

وَلَقَدۡ أَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ فَمَا ٱسۡتَكَانُواْ لِرَبِّهِمۡ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ

በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው፡፡ ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም፡፡ አይዋደቁምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
77 : 23

حَتَّىٰٓ إِذَا فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابٗا ذَا عَذَابٖ شَدِيدٍ إِذَا هُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ

በእነሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የኾነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
78 : 23

وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ

እርሱም ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
79 : 23

وَهُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ

እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው፡፡ ወደርሱም ትሰበሰባላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
80 : 23

وَهُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَلَهُ ٱخۡتِلَٰفُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

እርሱም ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው፡፡ አታውቁምን? info
التفاسير:

external-link copy
81 : 23

بَلۡ قَالُواْ مِثۡلَ مَا قَالَ ٱلۡأَوَّلُونَ

ይልቁንም (የመካ ከሓዲዎች) የፊተኞቹ ሕዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
82 : 23

قَالُوٓاْ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ

«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶች በኾን ጊዜ እኛ ተቀስቃሾች ነን?» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
83 : 23

لَقَدۡ وُعِدۡنَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا هَٰذَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

«ይህንን እኛም ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
84 : 23

قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
85 : 23

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

«በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን?» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
86 : 23

قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ

«የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
87 : 23

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ

«በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
88 : 23

قُلۡ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

«የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
89 : 23

سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ

«በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው፡፡ info
التفاسير: