Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
131 : 7

فَإِذَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡحَسَنَةُ قَالُواْ لَنَا هَٰذِهِۦۖ وَإِن تُصِبۡهُمۡ سَيِّئَةٞ يَطَّيَّرُواْ بِمُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓۗ أَلَآ إِنَّمَا طَٰٓئِرُهُمۡ عِندَ ٱللَّهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

131. ምቾት በመጣችላቸው ጊዜ «ይህች ለእኛ ተገቢ ናት።» ይላሉ። ክፋት ባገኛቸው ጊዜ ግን ሙሳና አብረውት ያሉት ክፉ ገዶቻቸው እንደሆኑ ያስባሉ። አስተውሉ! ክፉ እድላቸው (ገደቢስነታቸው) ከአላህ ዘንድ ነው:: አብዛኞቻቸው ግን ይህን አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
132 : 7

وَقَالُواْ مَهۡمَا تَأۡتِنَا بِهِۦ مِنۡ ءَايَةٖ لِّتَسۡحَرَنَا بِهَا فَمَا نَحۡنُ لَكَ بِمُؤۡمِنِينَ

132. «በማንኛይቱም ተዓምር ልትደግምብን ብታመጣም የምናምንልህ አይደለንም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
133 : 7

فَأَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلطُّوفَانَ وَٱلۡجَرَادَ وَٱلۡقُمَّلَ وَٱلضَّفَادِعَ وَٱلدَّمَ ءَايَٰتٖ مُّفَصَّلَٰتٖ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمٗا مُّجۡرِمِينَ

133. ወዲያዉም የውሃን ማጥለቅለቅ፤ አንበጣን፤ ቅማልን፤ እንቁራሪቶችን፤ ደምን፤ የተለያዩ ተዓምራት ሲሆኑ በእነርሱ ላይ ላክን:: እነርሱ ግን ኮሩም:: ተንኮለኞችም ህዝቦች ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
134 : 7

وَلَمَّا وَقَعَ عَلَيۡهِمُ ٱلرِّجۡزُ قَالُواْ يَٰمُوسَى ٱدۡعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَۖ لَئِن كَشَفۡتَ عَنَّا ٱلرِّجۡزَ لَنُؤۡمِنَنَّ لَكَ وَلَنُرۡسِلَنَّ مَعَكَ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

134. በእነርሱ ላይ ቅጣቱ በወደቀባቸውም ጊዜ «ሙሳ ሆይ! ጌታህን ላንተ ቃል ኪዳን በገባልህ መሠረት ለምንልንና ከእኛ ቅጣቱን ብታነሳልን ላንተ እናምንልሀለን:: የኢስራኢልን ልጆችም ካንተ ጋር እንለቃለን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
135 : 7

فَلَمَّا كَشَفۡنَا عَنۡهُمُ ٱلرِّجۡزَ إِلَىٰٓ أَجَلٍ هُم بَٰلِغُوهُ إِذَا هُمۡ يَنكُثُونَ

135. ለሚደርሱበት የተወሰነ ጊዜ ድረስ ቅጣትን ከእነርሱ ላይ ባነሳን ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ቃላቸውን አፈረሱ:: info
التفاسير:

external-link copy
136 : 7

فَٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡ فَأَغۡرَقۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡيَمِّ بِأَنَّهُمۡ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ عَنۡهَا غَٰفِلِينَ

136. እነርሱም በተዓምራታችን ስላስተባበሉና ከእርሷ ዘንጊዎች ስለሆኑ ተበቀልናቸው:: በባህር ውስጥም አሰመጥናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
137 : 7

وَأَوۡرَثۡنَا ٱلۡقَوۡمَ ٱلَّذِينَ كَانُواْ يُسۡتَضۡعَفُونَ مَشَٰرِقَ ٱلۡأَرۡضِ وَمَغَٰرِبَهَا ٱلَّتِي بَٰرَكۡنَا فِيهَاۖ وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلۡحُسۡنَىٰ عَلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ بِمَا صَبَرُواْۖ وَدَمَّرۡنَا مَا كَانَ يَصۡنَعُ فِرۡعَوۡنُ وَقَوۡمُهُۥ وَمَا كَانُواْ يَعۡرِشُونَ

137. እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ህዝቦች ያቺን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምስራቋንም ምዕራቧንም አወረስናቸው:: መልዕክተኛችን ሆይ! የጌታህ መልካሚቱ ቃል በኢስራኢል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች:: ፈርዖንና ሰዎቹ ይሰሩት የነበረውን ህንጻና ዳስ ያደርጉት የነበረውንም አፈረስን:: info
التفاسير: