Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
7 : 58

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ مَا يَكُونُ مِن نَّجۡوَىٰ ثَلَٰثَةٍ إِلَّا هُوَ رَابِعُهُمۡ وَلَا خَمۡسَةٍ إِلَّا هُوَ سَادِسُهُمۡ وَلَآ أَدۡنَىٰ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكۡثَرَ إِلَّا هُوَ مَعَهُمۡ أَيۡنَ مَا كَانُواْۖ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُواْ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٌ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? (በእውነቱ ሁሉንም አካቧል::) የሶስት ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም፤ አላህ አራተኛው ቢሆን እንጂ፤ የአምስትም ሰዎች መንሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ስድስተኛ ቢሆን እንጂ፤ ከዚያ ያነሰም ይሁን የበዛ ሰው መሾካሾክ አይከሰትም እርሱ ባሉበት ቦታ አብሯቸው ቢሆን እንጂ:: ከዚያ በትንሳኤ ቀን የሰሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል:: አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 58

أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ نُهُواْ عَنِ ٱلنَّجۡوَىٰ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا نُهُواْ عَنۡهُ وَيَتَنَٰجَوۡنَ بِٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِ وَمَعۡصِيَتِ ٱلرَّسُولِۖ وَإِذَا جَآءُوكَ حَيَّوۡكَ بِمَا لَمۡ يُحَيِّكَ بِهِ ٱللَّهُ وَيَقُولُونَ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ لَوۡلَا يُعَذِّبُنَا ٱللَّهُ بِمَا نَقُولُۚ حَسۡبُهُمۡ جَهَنَّمُ يَصۡلَوۡنَهَاۖ فَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ

8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በመጥፎ ነገር ከመመሳጠር ወደ ተከለከሉት፤ ከዚያ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር የሚመለሱትንና በኃጢአት፣ በጠላትነትና መልዕክተኛውን በመቃወም ወደ ሚመሳጠሩ አላየህምን? (ሰላም ሊሉ) ወደ አንተ በመጡ ጊዜ አላህ ባላናገረህ ቃል ያናግሩሃል:: ውስጣቸው ይህ ሰው ነብይ ከሆነ በምንለው ነገር አላህ አይቀጣንም ኖሯልን? (ነብይ ከሆነስ) የለመነውን ነገር አላህ ተቀብሎት በሞትን ነበር ይላሉ:: ገሀነም የሚገቡባት ሲሆኑ ከአሁኑ ሞት ይልቅ በቂያቸው ናት:: ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች! info
التفاسير:

external-link copy
9 : 58

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا تَنَٰجَيۡتُمۡ فَلَا تَتَنَٰجَوۡاْ بِٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِ وَمَعۡصِيَتِ ٱلرَّسُولِ وَتَنَٰجَوۡاْ بِٱلۡبِرِّ وَٱلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ ٱلَّذِيٓ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ

9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተመሳጠራችሁ ጊዜ በኃጢአት ወሰንን በማለፍና መልዕክተኛውንም በመቃወም አትሾካሾኩ ግን በበጎ ስራና አላህን በመፍራት ተወያዩ:: ያንንም ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 58

إِنَّمَا ٱلنَّجۡوَىٰ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ لِيَحۡزُنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَلَيۡسَ بِضَآرِّهِمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

10. በመጥፎ መመሳጠር ከሰይጣን ማስዋብና ማሳመር የሚመጣ ብቻ ነው:: እነዚያ ያመኑ ሙስሊሞች ያዝኑ ዘንድ ይቀሰቅሰዋል:: ከአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር የሰይጣንም መመሳጠር በምንም ነገር አይጎዳቸዉም:: እናም ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 58

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا قِيلَ لَكُمۡ تَفَسَّحُواْ فِي ٱلۡمَجَٰلِسِ فَٱفۡسَحُواْ يَفۡسَحِ ٱللَّهُ لَكُمۡۖ وَإِذَا قِيلَ ٱنشُزُواْ فَٱنشُزُواْ يَرۡفَعِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ دَرَجَٰتٖۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

11. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ ስፍራን አስፉ:: አላህ በገነት ያሰፋላችኃልና:: ተነሱ በተባለም ጊዜ ተነሱ:: አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን በትክክል ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች (በዚች ዓለምም ሆነ በአኼራ) ከፍ ያደርጋል:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አወቂ ነውና:: info
التفاسير: