Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
48 : 43

وَمَا نُرِيهِم مِّنۡ ءَايَةٍ إِلَّا هِيَ أَكۡبَرُ مِنۡ أُخۡتِهَاۖ وَأَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ

48. ከተዓምራት አንዲትንም እናሳያቸዉም እርሷ ከብጤዋ በጣም የበለጠች ብትሆን እንጅ። ከክህደታቸው ይመለሱም ዘንድ በቅጣት ያዝናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 43

وَقَالُواْ يَٰٓأَيُّهَ ٱلسَّاحِرُ ٱدۡعُ لَنَا رَبَّكَ بِمَا عَهِدَ عِندَكَ إِنَّنَا لَمُهۡتَدُونَ

49. አንተ ድግምተኛ ሆይ! «ጌታህን አንተ ዘንድ ቃል በገባልህ ለእኛ ለምንልን እኛ (ቅጣቱን ቢያነሳልን) ተመሪዎች ነን» አሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 43

فَلَمَّا كَشَفۡنَا عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابَ إِذَا هُمۡ يَنكُثُونَ

50. ስቃዩን ከእነርሱ ላይ በገለጥንም ጊዜ ወዲያውኑ ቃልኪዳናቸውን ያፈርሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 43

وَنَادَىٰ فِرۡعَوۡنُ فِي قَوۡمِهِۦ قَالَ يَٰقَوۡمِ أَلَيۡسَ لِي مُلۡكُ مِصۡرَ وَهَٰذِهِ ٱلۡأَنۡهَٰرُ تَجۡرِي مِن تَحۡتِيٓۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ

51. ፈርዖንም በህዝቦቹ ውስጥ ተጣራ። (እንዲህ) አለም: «ህዝቦቼ ሆይ! የሚስር (ግብጽ) ግዛት የእኔ አይደለምን? እነዚህም ጅረቶች ከስሬ የሚፈሱ ሲሆኑ የእኔ አይደሉምን? አትመለከቱምን? info
التفاسير:

external-link copy
52 : 43

أَمۡ أَنَا۠ خَيۡرٞ مِّنۡ هَٰذَا ٱلَّذِي هُوَ مَهِينٞ وَلَا يَكَادُ يُبِينُ

52. «በእውነት እኔ ከዚያ ያ እርሱ ወራዳ ጉዳዩንም በደንብ ሊገልጽ የማይችል ከሆነው ሰው በላጭ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
53 : 43

فَلَوۡلَآ أُلۡقِيَ عَلَيۡهِ أَسۡوِرَةٞ مِّن ذَهَبٍ أَوۡ جَآءَ مَعَهُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ مُقۡتَرِنِينَ

53. «እርሱ ላይ የወርቅ አንባሮች ለምን አልተጣሉበትም? ወይም መላዕክት ከእርሱ ጋር ተቆራኝተው ለምን አልመጡም?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
54 : 43

فَٱسۡتَخَفَّ قَوۡمَهُۥ فَأَطَاعُوهُۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ

54. ህዝቦቹንም አቄላቸው:: ታዘዙትም:: እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 43

فَلَمَّآ ءَاسَفُونَا ٱنتَقَمۡنَا مِنۡهُمۡ فَأَغۡرَقۡنَٰهُمۡ أَجۡمَعِينَ

55. ባስቆጡንም ጊዜ ከእነርሱ ተበቀልን:: ሁሉንም አሰመጥናቸውም:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 43

فَجَعَلۡنَٰهُمۡ سَلَفٗا وَمَثَلٗا لِّلۡأٓخِرِينَ

56. በጥፋት ቀዳሚዎችና ለኋለኞች መቀጣጫ ምሳሌም አደረግናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 43

۞ وَلَمَّا ضُرِبَ ٱبۡنُ مَرۡيَمَ مَثَلًا إِذَا قَوۡمُكَ مِنۡهُ يَصِدُّونَ

57. የመርየም ልጅ ዒሳ ምሳሌ በተደረገ ጊዜ ህዝቦችህ (ከሀዲያኑ) ወዲያውኑ ከእርሱ ሌሎችን ያግዳሉ። info
التفاسير:

external-link copy
58 : 43

وَقَالُوٓاْ ءَأَٰلِهَتُنَا خَيۡرٌ أَمۡ هُوَۚ مَا ضَرَبُوهُ لَكَ إِلَّا جَدَلَۢاۚ بَلۡ هُمۡ قَوۡمٌ خَصِمُونَ

58. «አማልክቶቻችን ይበልጣሉን? ወይስ እርሱ ይበልጣል?» አሉም:: ለክርክር እንጅ ላንተ (እርሱን) ምሳሌ አላደረጉትም:: በእውነት እነርሱ ክርክረ ብርቱ ህዝቦች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
59 : 43

إِنۡ هُوَ إِلَّا عَبۡدٌ أَنۡعَمۡنَا عَلَيۡهِ وَجَعَلۡنَٰهُ مَثَلٗا لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

59. እርሱ (ዒሳ) በእርሱ ላይ የለገስንለት ለኢስራኢል ልጆችም ተዐምር ያደረግነው አገልጋይ ባሪያችን እንጂ ሌላ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 43

وَلَوۡ نَشَآءُ لَجَعَلۡنَا مِنكُم مَّلَٰٓئِكَةٗ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَخۡلُفُونَ

60. ብንፈልግም ኖሮ በምድር ላይ በእናንተ ምትክ መላዕክትን ባደረግን ነበር:: info
التفاسير: