Traducción de los significados del Sagrado Corán - Traducción al amárico - Academia de África

Número de página:close

external-link copy
26 : 10

۞ لِّلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ ٱلۡحُسۡنَىٰ وَزِيَادَةٞۖ وَلَا يَرۡهَقُ وُجُوهَهُمۡ قَتَرٞ وَلَا ذِلَّةٌۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

26. ለእነዚያ መልካም ለሠሩት ሰዎች መልካም ነገርና (ገነት) ሌላ ተጨማሪም አላቸው:: ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸዉም:: እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 10

وَٱلَّذِينَ كَسَبُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ جَزَآءُ سَيِّئَةِۭ بِمِثۡلِهَا وَتَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۖ مَّا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنۡ عَاصِمٖۖ كَأَنَّمَآ أُغۡشِيَتۡ وُجُوهُهُمۡ قِطَعٗا مِّنَ ٱلَّيۡلِ مُظۡلِمًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ

27. እነዚያ ኃጢአቶችን የሠሩት ደግሞ ኃጢአቲቱን የሚመጥን ቅጣት አለባቸው:: ውርደትም ትሸፍናቸዋለች :: እነርሱ ከአላህ ቅጣት ጠባቂ የላቸዉም:: ፊቶቻቸው በድቅድቅ ጨለማ ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይሆናሉ:: እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 10

وَيَوۡمَ نَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ مَكَانَكُمۡ أَنتُمۡ وَشُرَكَآؤُكُمۡۚ فَزَيَّلۡنَا بَيۡنَهُمۡۖ وَقَالَ شُرَكَآؤُهُم مَّا كُنتُمۡ إِيَّانَا تَعۡبُدُونَ

28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አማልክትንና አምላኪዎቻቸውን ሁሉ በአንድ የምንሰበስባቸውንና ከዚያም ለእነዚያ ላጋሩት «እናንተም ተጋሪዎቻችሁም ቦታችሁን ያዙ።» የምንልበትን ተጋሪዎቻቸዉም (እንዲህ) የሚሏቸው ሲሆኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን አስታውስ «ትገዙ የነበረው እኛን አልነበረም። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 10

فَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدَۢا بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمۡ إِن كُنَّا عَنۡ عِبَادَتِكُمۡ لَغَٰفِلِينَ

29. (ጣኦታቶቹ) «እኛን ለመገዛታችሁ ዘንጊዎች ለመሆናችን በኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ።» ይሏቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 10

هُنَالِكَ تَبۡلُواْ كُلُّ نَفۡسٖ مَّآ أَسۡلَفَتۡۚ وَرُدُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ مَوۡلَىٰهُمُ ٱلۡحَقِّۖ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

30. በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች:: አጋሪዎች ወደ አላህ እውነተኛ ወደሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ:: ያ በአላህ ላይ ይቀጣጥፋት የነበሩት ሁሉ ነገርም ይጠፋባቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 10

قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن يَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَمَن يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ

31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረላችሁ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ፤ ከህያዉም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው:: «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል:: «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ? ታዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 10

فَذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَاذَا بَعۡدَ ٱلۡحَقِّ إِلَّا ٱلضَّلَٰلُۖ فَأَنَّىٰ تُصۡرَفُونَ

32. እውነተኛው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው:: ከእውነት በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ? ከእውነት እንዴት ትዞራላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
33 : 10

كَذَٰلِكَ حَقَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ فَسَقُوٓاْ أَنَّهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

33. ልክ እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ሰዎች ላይ ፈጽሞ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠ:: info
التفاسير: