Translation of the Meanings of the Noble Qur'an - Amharic translation - Africa Academy

Page Number:close

external-link copy
84 : 5

وَمَا لَنَا لَا نُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَمَا جَآءَنَا مِنَ ٱلۡحَقِّ وَنَطۡمَعُ أَن يُدۡخِلَنَا رَبُّنَا مَعَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلصَّٰلِحِينَ

84. «ጌታችን ከመልካም ሰሪዎች ጋር ገነትን ሊያስገባን የምንከጅል ስንሆን በአላህና ከእርሱ በመጣልን እውነት ሁሉ የማናምንበት ምን ምክንያት አለን?» (ይላሉ።) info
التفاسير:

external-link copy
85 : 5

فَأَثَٰبَهُمُ ٱللَّهُ بِمَا قَالُواْ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ وَذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلۡمُحۡسِنِينَ

85. እናም ባሉት ምክንያት አላህ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችን በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ መነዳቸው። ይህም የበጎ ሰሪዎች ዋጋ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
86 : 5

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَحِيمِ

86. እነዚያም የካዱና በአናቅጻችን ያስተባበሉ ሁሉ የእሳት ጓዶች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
87 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُحَرِّمُواْ طَيِّبَٰتِ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكُمۡ وَلَا تَعۡتَدُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُعۡتَدِينَ

87. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለእናንተ የፈቀደላችሁን ጣፋጮች በራሳችሁ ላይ እርም አታድርጉ:: ወሰንንም አትለፉ:: አላህ ወሰን አላፊዎችን ሁሉ አይወድምና:: info
التفاسير:

external-link copy
88 : 5

وَكُلُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ حَلَٰلٗا طَيِّبٗاۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ ٱلَّذِيٓ أَنتُم بِهِۦ مُؤۡمِنُونَ

88. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደ ጥሩ ሲሆን ብሉ። ያንን ያመናችሁበት ጌታችሁን አላህንም ፍሩ። info
التفاسير:

external-link copy
89 : 5

لَا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغۡوِ فِيٓ أَيۡمَٰنِكُمۡ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ ٱلۡأَيۡمَٰنَۖ فَكَفَّٰرَتُهُۥٓ إِطۡعَامُ عَشَرَةِ مَسَٰكِينَ مِنۡ أَوۡسَطِ مَا تُطۡعِمُونَ أَهۡلِيكُمۡ أَوۡ كِسۡوَتُهُمۡ أَوۡ تَحۡرِيرُ رَقَبَةٖۖ فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٖۚ ذَٰلِكَ كَفَّٰرَةُ أَيۡمَٰنِكُمۡ إِذَا حَلَفۡتُمۡۚ وَٱحۡفَظُوٓاْ أَيۡمَٰنَكُمۡۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

89. (ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ከመሀሎቻችሁ መካከል በውድቁ አይዛችሁም:: ባሰባችሁበት መሀላ ግን ይይዛችኋል:: እናም መሀላዎችን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ለአስር ሚስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይም የአንዲትን ባሪያ ጫንቃን ነፃ ማውጣት ነው:: ከተባሉት አንዱንም ያለገኘ ሶስት ቀናትን መፆም ብቻ ነው:: ይህ በማላችሁና መሀላዎቻችሁን ባፈረሳችሁ ጊዜ ማሰረዣው ነው:: መሀላዎቻችሁንም ጠብቁ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አናቅጽን ያብራራል:: እናንተም ልታመሰግኑት ይከጀላልና:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّمَا ٱلۡخَمۡرُ وَٱلۡمَيۡسِرُ وَٱلۡأَنصَابُ وَٱلۡأَزۡلَٰمُ رِجۡسٞ مِّنۡ عَمَلِ ٱلشَّيۡطَٰنِ فَٱجۡتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ

90. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፤ የቁማር ጫዎታ፤ ጣዖታትን መገዛት እና አዝላምም ከሰይጣን ስራ የሆነ እና እርኩስ ተግባር ብቻ ናቸው። ትድኑ ዘንድም ራቁት። info
التفاسير: