Translation of the Meanings of the Noble Qur'an - Amharic translation - Africa Academy

አል-በቀራህ

external-link copy
1 : 2

الٓمٓ

1. አሊፍ ፤ ላም፤ ሚም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 2

ذَٰلِكَ ٱلۡكِتَٰبُ لَا رَيۡبَۛ فِيهِۛ هُدٗى لِّلۡمُتَّقِينَ

2. ይህ መጽሐፍ (ቁርኣን) (ከአላህ የተወረደ ለመሆኑ) ምንም ጥርጥር የለበትም:: አላህን ለሚፈሩም ሁሉ መመሪያ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 2

ٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡغَيۡبِ وَيُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ يُنفِقُونَ

3. ለእነዚያ በሩቁ ነገር ለሚያምኑት፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ለሚሰግዱት፤ ከሰጠናቸዉ ሲሳይም ለሚለግሱ። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 2

وَٱلَّذِينَ يُؤۡمِنُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبۡلِكَ وَبِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ يُوقِنُونَ

4. ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደው መጽሐፍና ካንተ በፊትም በተወረዱት መጽሐፍት ሁሉ ለሚያምኑ፤ በመጨረሻው ቀን መኖርም ለሚያረጋግጡ ሰዎች ሁሉ (መመሪያ ነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 2

أُوْلَٰٓئِكَ عَلَىٰ هُدٗى مِّن رَّبِّهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ በትክክል የሚጓዙ ናቸው:: ፍላጎታቸውን ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ info
التفاسير: