Translation of the Meanings of the Noble Qur'an - Amharic translation - Muhammad Sadiq

አል ዐለቅ

external-link copy
1 : 96

ٱقۡرَأۡ بِٱسۡمِ رَبِّكَ ٱلَّذِي خَلَقَ

አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡{1} info

{1} ይህ አንቀጽና ቀጥሎ ያሉት ከቁርአን መጀመሪያ የወረዱ አንቀጾች ናቸው። በኑር ተራራ ላይ በምገኘው የሂራእ ዋሻ ውስጥ ነቢዩ ሰ/ዐ/ወ/ ኸልዋ ወጥተው እያሉ ነው የወረደባቸው። (ቡኻሪና ሙስሊም፤ የወህይ አጀማመር ምእራፍ)

التفاسير:

external-link copy
2 : 96

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِنۡ عَلَقٍ

ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 96

ٱقۡرَأۡ وَرَبُّكَ ٱلۡأَكۡرَمُ

አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 96

ٱلَّذِي عَلَّمَ بِٱلۡقَلَمِ

ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 96

عَلَّمَ ٱلۡإِنسَٰنَ مَا لَمۡ يَعۡلَمۡ

ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 96

كَلَّآ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَيَطۡغَىٰٓ

በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 96

أَن رَّءَاهُ ٱسۡتَغۡنَىٰٓ

ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 96

إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلرُّجۡعَىٰٓ

መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 96

أَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي يَنۡهَىٰ

አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 96

عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰٓ

ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 96

أَرَءَيۡتَ إِن كَانَ عَلَى ٱلۡهُدَىٰٓ

አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 96

أَوۡ أَمَرَ بِٱلتَّقۡوَىٰٓ

ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 96

أَرَءَيۡتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰٓ

አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 96

أَلَمۡ يَعۡلَم بِأَنَّ ٱللَّهَ يَرَىٰ

አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን? info
التفاسير:

external-link copy
15 : 96

كَلَّا لَئِن لَّمۡ يَنتَهِ لَنَسۡفَعَۢا بِٱلنَّاصِيَةِ

ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 96

نَاصِيَةٖ كَٰذِبَةٍ خَاطِئَةٖ

ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 96

فَلۡيَدۡعُ نَادِيَهُۥ

ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 96

سَنَدۡعُ ٱلزَّبَانِيَةَ

(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 96

كَلَّا لَا تُطِعۡهُ وَٱسۡجُدۡۤ وَٱقۡتَرِب۩

ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ {1} info

{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ አለ። ይህ የመጨረሻ ሱጁድ ነው።

التفاسير: