Translation of the Meanings of the Noble Qur'an - Amharic translation - Muhammad Sadiq

አስ ሷፋት

external-link copy
1 : 37

وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ صَفّٗا

መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 37

فَٱلزَّٰجِرَٰتِ زَجۡرٗا

መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 37

فَٱلتَّٰلِيَٰتِ ذِكۡرًا

ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 37

إِنَّ إِلَٰهَكُمۡ لَوَٰحِدٞ

አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 37

رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَرَبُّ ٱلۡمَشَٰرِقِ

የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 37

إِنَّا زَيَّنَّا ٱلسَّمَآءَ ٱلدُّنۡيَا بِزِينَةٍ ٱلۡكَوَاكِبِ

እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 37

وَحِفۡظٗا مِّن كُلِّ شَيۡطَٰنٖ مَّارِدٖ

አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 37

لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى ٱلۡمَلَإِ ٱلۡأَعۡلَىٰ وَيُقۡذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٖ

ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 37

دُحُورٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ وَاصِبٌ

የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 37

إِلَّا مَنۡ خَطِفَ ٱلۡخَطۡفَةَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٞ ثَاقِبٞ

ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 37

فَٱسۡتَفۡتِهِمۡ أَهُمۡ أَشَدُّ خَلۡقًا أَم مَّنۡ خَلَقۡنَآۚ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّن طِينٖ لَّازِبِۭ

ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 37

بَلۡ عَجِبۡتَ وَيَسۡخَرُونَ

ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 37

وَإِذَا ذُكِّرُواْ لَا يَذۡكُرُونَ

በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 37

وَإِذَا رَأَوۡاْ ءَايَةٗ يَسۡتَسۡخِرُونَ

ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 37

وَقَالُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٌ

ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 37

أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ

«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን? info
التفاسير:

external-link copy
17 : 37

أَوَءَابَآؤُنَا ٱلۡأَوَّلُونَ

«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 37

قُلۡ نَعَمۡ وَأَنتُمۡ دَٰخِرُونَ

«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 37

فَإِنَّمَا هِيَ زَجۡرَةٞ وَٰحِدَةٞ فَإِذَا هُمۡ يَنظُرُونَ

እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 37

وَقَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا هَٰذَا يَوۡمُ ٱلدِّينِ

«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 37

هَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡفَصۡلِ ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تُكَذِّبُونَ

«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 37

۞ ٱحۡشُرُواْ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ وَأَزۡوَٰجَهُمۡ وَمَا كَانُواْ يَعۡبُدُونَ

(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 37

مِن دُونِ ٱللَّهِ فَٱهۡدُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطِ ٱلۡجَحِيمِ

«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 37

وَقِفُوهُمۡۖ إِنَّهُم مَّسۡـُٔولُونَ

«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡ info
التفاسير: