Translation of the Meanings of the Noble Qur'an - Amharic translation - Muhammad Sadiq

አል-ፋቲሃ

external-link copy
1 : 1

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡{1} info

{1} የመክፈቻይቱ ምእራፍ የቁርኣን በላጭ ሱራ ነች። ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ለአቢ ሰዒድ እንዲህ አሉ፡- “ከቁርኣን ሱራዎች ውስጥ በላጩን አሳውቅሃለሁ እርሱም አልሃምዱ ሊላሂ ረቢል ዓላሚን- ነው።" {ቡኻሪ ዘግበውታል}።

التفاسير:

external-link copy
2 : 1

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 1

ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 1

مَٰلِكِ يَوۡمِ ٱلدِّينِ

የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 1

إِيَّاكَ نَعۡبُدُ وَإِيَّاكَ نَسۡتَعِينُ

አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 1

ٱهۡدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ

ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 1

صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِمۡ غَيۡرِ ٱلۡمَغۡضُوبِ عَلَيۡهِمۡ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ

የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡ {1} info

{1} ኣሚን የምትል ቃል በሶላት ውስጥ እዚህ ትባላለች፤ እንደውም ድምጽ ከፍ በምደረግበት ሶላት ውስጥ ጀማኣው በአንድነት ድምጽ ከፍ ተደርጎ ማለት ያስፈልጋል። ግን እሷ ከፋትሃ አይደለችም።

التفاسير: