Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
9 : 62

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَوۡمِ ٱلۡجُمُعَةِ فَٱسۡعَوۡاْ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِ وَذَرُواْ ٱلۡبَيۡعَۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአርብ (በጁሙዓ) ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት (ኹጥባ፣ ሶላት) ተጣደፉ:: መሸጥንም ተው:: የምታውቁ ብትሆኑ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 62

فَإِذَا قُضِيَتِ ٱلصَّلَوٰةُ فَٱنتَشِرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَٱبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَثِيرٗا لَّعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ

10. ሶላቷ በተፈጸመችም ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑና የአላህን ችሮታ ፈልጉ:: ልትድኑ ይከጀላልና አላህንም በብዙው አውሱ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 62

وَإِذَا رَأَوۡاْ تِجَٰرَةً أَوۡ لَهۡوًا ٱنفَضُّوٓاْ إِلَيۡهَا وَتَرَكُوكَ قَآئِمٗاۚ قُلۡ مَا عِندَ ٱللَّهِ خَيۡرٞ مِّنَ ٱللَّهۡوِ وَمِنَ ٱلتِّجَٰرَةِۚ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ

11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተውህ ሲሆኑ ወደ እርሷ ይበተናሉ:: «አላህ ዘንድ ያለው ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው:: አላህም ከሰጭዎች ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጪ ነው» በላቸው:: info
التفاسير: