Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
19 : 6

قُلۡ أَيُّ شَيۡءٍ أَكۡبَرُ شَهَٰدَةٗۖ قُلِ ٱللَّهُۖ شَهِيدُۢ بَيۡنِي وَبَيۡنَكُمۡۚ وَأُوحِيَ إِلَيَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ لِأُنذِرَكُم بِهِۦ وَمَنۢ بَلَغَۚ أَئِنَّكُمۡ لَتَشۡهَدُونَ أَنَّ مَعَ ٱللَّهِ ءَالِهَةً أُخۡرَىٰۚ قُل لَّآ أَشۡهَدُۚ قُلۡ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞ وَإِنَّنِي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ

19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከምስክርነት ሁሉ ይበልጥ ታላቁ የትኛው ነው?» በላቸው። «አላህ፤ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው። ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውንም ሁሉ ላስፈራራበት ወደ እኔ ተወረደ:: ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላቸሁን?» በላቸው:: «እኔ ግን ፈጽሞ በዚህ አልመሰክርም።» በላቸው:: «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እኔም በአላህ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 6

ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَعۡرِفُونَهُۥ كَمَا يَعۡرِفُونَ أَبۡنَآءَهُمُۘ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

20. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው አይሁድና ክርስቲያኖች ልክ ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ ሙሐመድንም በትክክል ያውቁታል:: እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት እነርሱ ፈጽሞ አያምኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 6

وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ

21. በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአናቅጽ ካስተባበለ ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 6

وَيَوۡمَ نَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشۡرَكُوٓاْ أَيۡنَ شُرَكَآؤُكُمُ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ

22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁላቸውንም በምንሰበሰብበትና ከዚያም ለእነዚያም በአላህ ላጋሩት፤ «‹እነዚያም ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው› ብላችሁ ታስቧቸው የነበሩት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው?» የምንልበትን ቀን (አስታውስ)። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 6

ثُمَّ لَمۡ تَكُن فِتۡنَتُهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ وَٱللَّهِ رَبِّنَا مَا كُنَّا مُشۡرِكِينَ

23. ከዚያም የፊትና መልሳቸው «በጌታችን በአላህ ይሁንብን አጋሪዎች አልነበርንም።» ማለት እንጂ ሌላ አይሆንም። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 6

ٱنظُرۡ كَيۡفَ كَذَبُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡۚ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በነፍሶቻቸው ላይ እንዴት እንደዋሹና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ሁሉ ከእነርሱ እንዴት እንደተሰወረባቸው ተመልከት:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 6

وَمِنۡهُم مَّن يَسۡتَمِعُ إِلَيۡكَۖ وَجَعَلۡنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ أَكِنَّةً أَن يَفۡقَهُوهُ وَفِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٗاۚ وَإِن يَرَوۡاْ كُلَّ ءَايَةٖ لَّا يُؤۡمِنُواْ بِهَاۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوكَ يُجَٰدِلُونَكَ يَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

25. ከእነርሱ መካከል ወደ አንተ የሚያዳምጥ ሰው አለ:: በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሽፋኖችን፤ በጆሮዎቻቸዉም ላይ እንዳይሰሙት ድንቁርናን አደረግን:: ተዐምርን ሁሉ እንኳን ቢያዩ በእርሷ አያምኑም:: ወደ አንተ በመጡ ጊዜ የሚከራከሩህ ሆነው እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች «ይህ ቁርኣን የቀድሞዎቹ ሰዎች ጹሑፍ ተረቶች ስብስብ እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 6

وَهُمۡ يَنۡهَوۡنَ عَنۡهُ وَيَنۡـَٔوۡنَ عَنۡهُۖ وَإِن يُهۡلِكُونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ

26. እነርሱም ሰዎችን ከእርሱ ይከልክላሉ፤ ከእርሱም ይርቃሉ፤ በዚህም ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን አያጠፉም:: ግን አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 6

وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ وُقِفُواْ عَلَى ٱلنَّارِ فَقَالُواْ يَٰلَيۡتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእሳትም ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ጊዜ «ምን ነው ወደ ምድረ ዓለም በተመለስንና በጌታችን አናቅጽ ባላስተባበልን ከትክክለኛ አማኞችም ጋር በሆንን ዋ! ምኞታችን።» ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያስደነግጥህን ነገር ባየህ ነበር) info
التفاسير: