Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
7 : 54

خُشَّعًا أَبۡصَٰرُهُمۡ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ كَأَنَّهُمۡ جَرَادٞ مُّنتَشِرٞ

7. ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነውና ፍጹም የተበተኑ አንበጣ መስለው ከየመቃብሮቻቸው ይወጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 54

مُّهۡطِعِينَ إِلَى ٱلدَّاعِۖ يَقُولُ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا يَوۡمٌ عَسِرٞ

8. ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎችና ቸኳዩች ሆነው ይወጣሉ:: ከሓዲያን ያን ጊዜ «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 54

۞ كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ فَكَذَّبُواْ عَبۡدَنَا وَقَالُواْ مَجۡنُونٞ وَٱزۡدُجِرَ

9. ከእነርሱ በፊት የ(ነብዩ) ኑህ ህዝቦች አስተባበሉ:: ባሪያችንንም ኑህን አስተባበሉ:: «ዕብድ ነዉም» አሉት:: ተገላመጠም:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 54

فَدَعَا رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَغۡلُوبٞ فَٱنتَصِرۡ

10. «ጌታውንም እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ተጣራ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 54

فَفَتَحۡنَآ أَبۡوَٰبَ ٱلسَّمَآءِ بِمَآءٖ مُّنۡهَمِرٖ

11. ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 54

وَفَجَّرۡنَا ٱلۡأَرۡضَ عُيُونٗا فَٱلۡتَقَى ٱلۡمَآءُ عَلَىٰٓ أَمۡرٖ قَدۡ قُدِرَ

12. የምድርንም ምንጮች በሃይል አፈነዳን:: የሰማዩና የምድሩ ውሃዉም ቀድሞ በተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 54

وَحَمَلۡنَٰهُ عَلَىٰ ذَاتِ أَلۡوَٰحٖ وَدُسُرٖ

13. ባለ ብዙ ሳንቃዎችና ባለ ብዙ ሚስማሮች በሆነቸው ታንኳ ላይም ጫንነው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 54

تَجۡرِي بِأَعۡيُنِنَا جَزَآءٗ لِّمَن كَانَ كُفِرَ

14. በጥበቃችን ስር ሆና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረ ሰው ምንዳ ይህን ሰራን። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 54

وَلَقَد تَّرَكۡنَٰهَآ ءَايَةٗ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

15. ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት:: ተገሳጭ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
16 : 54

فَكَيۡفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

16. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ? info
التفاسير:

external-link copy
17 : 54

وَلَقَدۡ يَسَّرۡنَا ٱلۡقُرۡءَانَ لِلذِّكۡرِ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

17. ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገንዛቢ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
18 : 54

كَذَّبَتۡ عَادٞ فَكَيۡفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

18. የዓድ ህዝቦች አስተባበሉ:: ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ፤ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 54

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِيحٗا صَرۡصَرٗا فِي يَوۡمِ نَحۡسٖ مُّسۡتَمِرّٖ

19. እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በሆነ ቀን በኃይል የምንትሻሻ ነፋስን ላክንባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 54

تَنزِعُ ٱلنَّاسَ كَأَنَّهُمۡ أَعۡجَازُ نَخۡلٖ مُّنقَعِرٖ

20. ሰዎችንም ልክ ከስሮቻቸው እንደተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከየተደበቁበት ትነቅላቸዋለች:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 54

فَكَيۡفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

21. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 54

وَلَقَدۡ يَسَّرۡنَا ٱلۡقُرۡءَانَ لِلذِّكۡرِ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

22. ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
23 : 54

كَذَّبَتۡ ثَمُودُ بِٱلنُّذُرِ

23. የሰሙድ ህዝቦች በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 54

فَقَالُوٓاْ أَبَشَرٗا مِّنَّا وَٰحِدٗا نَّتَّبِعُهُۥٓ إِنَّآ إِذٗا لَّفِي ضَلَٰلٖ وَسُعُرٍ

24. (እንዲህም) አሉ: «ከእኛ የሆነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያ! ጊዜ በስህተትና በእብደት ውስጥ ነን አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 54

أَءُلۡقِيَ ٱلذِّكۡرُ عَلَيۡهِ مِنۢ بَيۡنِنَا بَلۡ هُوَ كَذَّابٌ أَشِرٞ

25. «ከእኛ መካከል በእርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራዕይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 54

سَيَعۡلَمُونَ غَدٗا مَّنِ ٱلۡكَذَّابُ ٱلۡأَشِرُ

26. ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 54

إِنَّا مُرۡسِلُواْ ٱلنَّاقَةِ فِتۡنَةٗ لَّهُمۡ فَٱرۡتَقِبۡهُمۡ وَٱصۡطَبِرۡ

27. እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን:: ተጠባበቃቸዉም ታገስም:: info
التفاسير: