Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

አል አህቃፍ

external-link copy
1 : 46

حمٓ

1. ሓ፤ ሚይም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 46

تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ

2. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ፤ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 46

مَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ عَمَّآ أُنذِرُواْ مُعۡرِضُونَ

3. ሰማያትን፤ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በምር እና በተወሰነ ጊዜንም በመለካት እንጂ ለቀልድ አልፈጠርናቸዉም። እነዚያ በአላህ የካዱት የተስፈራሩትን ነገር ደንታ አይሰጡትም። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 46

قُلۡ أَرَءَيۡتُم مَّا تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُواْ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ لَهُمۡ شِرۡكٞ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِۖ ٱئۡتُونِي بِكِتَٰبٖ مِّن قَبۡلِ هَٰذَآ أَوۡ أَثَٰرَةٖ مِّنۡ عِلۡمٍ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

4. (መልዕክተኛችንሙሐመድ ሆይ!) «ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አላያችሁምን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ እስቲ አሳዩኝ:: ወይስ በሰማያት መፍጠር ለእነርሱ ከአላህ ጋር መጋራት አላቸውን? (ያማልዱናል በማለታችሁ) እውነተኞች እንደሆናችሁ ይህንን ጉዳይ ከዚህ በፊት የሆነን መጽሐፍ ወይም ከእውቀት ቅሪት እስቲ አምጡልኝ» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 46

وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن يَدۡعُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسۡتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَآئِهِمۡ غَٰفِلُونَ

5. እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልሱለትን ጣዖታት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማንነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው:: info
التفاسير: