Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
87 : 4

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ لَيَجۡمَعَنَّكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِۗ وَمَنۡ أَصۡدَقُ مِنَ ٱللَّهِ حَدِيثٗا

87. አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላከ የለም:: ወደ ትንሳኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን በእርግጥ ይሰበስባችኋል:: በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው? info
التفاسير:

external-link copy
88 : 4

۞ فَمَا لَكُمۡ فِي ٱلۡمُنَٰفِقِينَ فِئَتَيۡنِ وَٱللَّهُ أَرۡكَسَهُم بِمَا كَسَبُوٓاْۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَهۡدُواْ مَنۡ أَضَلَّ ٱللَّهُۖ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلٗا

88.(አማኞች ሆይ) አላህ በስራዎቻቸው ምክንያት ወደ ክህደት የመለሳቸው ሲሆኑ በሙናፊቆች ጉዳይ እናንተ ለሁለት ቡድን የተከፈላችሁት ምን ሆናችሁ ነው? አላህ ያጠመመውን ሰው ልታቀኑ ታስባላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያጠመመውን ሰው ለእርሱ መንገድ ፈጽሞ አታገኝለትም:: info
التفاسير:

external-link copy
89 : 4

وَدُّواْ لَوۡ تَكۡفُرُونَ كَمَا كَفَرُواْ فَتَكُونُونَ سَوَآءٗۖ فَلَا تَتَّخِذُواْ مِنۡهُمۡ أَوۡلِيَآءَ حَتَّىٰ يُهَاجِرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَخُذُوهُمۡ وَٱقۡتُلُوهُمۡ حَيۡثُ وَجَدتُّمُوهُمۡۖ وَلَا تَتَّخِذُواْ مِنۡهُمۡ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرًا

89. (አማኞች ሆይ) በአላህ እንደ ካዱ ሁሉ እናንተም እንድትክዱና ከእነርሱ ጋር እኩል እንድትሆኑ ተመኙ:: በአላህ መንገድ እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ መካከል ወዳጆችን አትያዙ:: ከእምነት ካፈገፈጉም ማርኳቸው:: ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ከእነርሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 4

إِلَّا ٱلَّذِينَ يَصِلُونَ إِلَىٰ قَوۡمِۭ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُم مِّيثَٰقٌ أَوۡ جَآءُوكُمۡ حَصِرَتۡ صُدُورُهُمۡ أَن يُقَٰتِلُوكُمۡ أَوۡ يُقَٰتِلُواْ قَوۡمَهُمۡۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَسَلَّطَهُمۡ عَلَيۡكُمۡ فَلَقَٰتَلُوكُمۡۚ فَإِنِ ٱعۡتَزَلُوكُمۡ فَلَمۡ يُقَٰتِلُوكُمۡ وَأَلۡقَوۡاْ إِلَيۡكُمُ ٱلسَّلَمَ فَمَا جَعَلَ ٱللَّهُ لَكُمۡ عَلَيۡهِمۡ سَبِيلٗا

90. እነዚያ በእናተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ወዳላቸው ህዝቦች የሚጠጉ፤ ወይም እናንተን ለመጋደልም ይሁን ወገኖቻቸውን ለመጋደል ልቦቻቸው የተጨነቁ ሆነው ወደ እናንተ የመጡ ሲቀሩ እነዚያንማ አትጋደሏቸው:: አላህ በፈለገ ኖሮ በእናንተ ላይ ሀይል በሰጣቸውና በተዋጓችሁ ነበር:: ቢተዋችሁ ባይዋጓችሁ ወደ እናንተ የእርቅን ሀሳብ ቢያቀርቡ አላህ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የመዋጋት መንገድን አላደረገም:: info
التفاسير:

external-link copy
91 : 4

سَتَجِدُونَ ءَاخَرِينَ يُرِيدُونَ أَن يَأۡمَنُوكُمۡ وَيَأۡمَنُواْ قَوۡمَهُمۡ كُلَّ مَا رُدُّوٓاْ إِلَى ٱلۡفِتۡنَةِ أُرۡكِسُواْ فِيهَاۚ فَإِن لَّمۡ يَعۡتَزِلُوكُمۡ وَيُلۡقُوٓاْ إِلَيۡكُمُ ٱلسَّلَمَ وَيَكُفُّوٓاْ أَيۡدِيَهُمۡ فَخُذُوهُمۡ وَٱقۡتُلُوهُمۡ حَيۡثُ ثَقِفۡتُمُوهُمۡۚ وَأُوْلَٰٓئِكُمۡ جَعَلۡنَا لَكُمۡ عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٗا مُّبِينٗا

91. ከናንተም ሆነ ከወገኖቻቸው ለመዳን የሚፈልጉ ሌሎች ቡድኖችም ታገኛላችሁ:: ወደ እውከት እንዲመለሱ በተጠሩ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይዘፈቃሉ:: ባይተዋችሁና እርቅን ካላቀረቡላችሁ እጆቻቸውንም ባይሰበስቡ ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ማርኳቸው:: ግደሏቸዉም:: እነዚያን ለእናንተ በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን አድርገንላችኋል:: info
التفاسير: