Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

ሷድ

external-link copy
1 : 38

صٓۚ وَٱلۡقُرۡءَانِ ذِي ٱلذِّكۡرِ

1. ሷድ፤ የግሳፄ ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 38

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فِي عِزَّةٖ وَشِقَاقٖ

2. ይልቁንም እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች በከባድ ትዕቢትና በአጓጉል ክርክር ውስጥ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 38

كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّن قَرۡنٖ فَنَادَواْ وَّلَاتَ حِينَ مَنَاصٖ

3. ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙን አጥፍተናል:: ጊዜው የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 38

وَعَجِبُوٓاْ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٞ مِّنۡهُمۡۖ وَقَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٞ كَذَّابٌ

4. ከእነርሱ መካከል የሆነ አስፈራሪ ስለመጣላቸውም ተደነቁ:: ከሓዲያንም አሉ: «ይህ ድግምተኛ ጠንቋይ ውሸታም ነው። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 38

أَجَعَلَ ٱلۡأٓلِهَةَ إِلَٰهٗا وَٰحِدًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عُجَابٞ

5. «አማልዕክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 38

وَٱنطَلَقَ ٱلۡمَلَأُ مِنۡهُمۡ أَنِ ٱمۡشُواْ وَٱصۡبِرُواْ عَلَىٰٓ ءَالِهَتِكُمۡۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٞ يُرَادُ

6. ከእነርሱም መካከል ባላባቶቹ (እንዲህ) እያሉ አዘገሙ: «ሂዱ በአማልክቶቻችሁም መገዛት ላይ ጽኑ:: ይህ ከእኛ የሚፈለግ ነገር ነውና info
التفاسير:

external-link copy
7 : 38

مَا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِي ٱلۡمِلَّةِ ٱلۡأٓخِرَةِ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا ٱخۡتِلَٰقٌ

7. «ይህንንም አስተምህሮት ከኋለኛይቱ (ከመጨረሻይቱ) ሃይማኖት አልሰማንም:: ይህ ውሸትን መፍጠር እንጂ ሌላ አይደለም። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 38

أَءُنزِلَ عَلَيۡهِ ٱلذِّكۡرُ مِنۢ بَيۡنِنَاۚ بَلۡ هُمۡ فِي شَكّٖ مِّن ذِكۡرِيۚ بَل لَّمَّا يَذُوقُواْ عَذَابِ

8. «ከመካከላችን በእርሱ ላይ ብቻ ቁርኣን ተወረደን?» (እያሉ አዘገሙ።) ይልቁን እነርሱ ከግሳጼየ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: በእርግጥም ቅጣትን ገና አልቀመሱም:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 38

أَمۡ عِندَهُمۡ خَزَآئِنُ رَحۡمَةِ رَبِّكَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡوَهَّابِ

9. ወይስ የአሸናፊውና የለጋሹ ጌታህ የአላህ የችሮታው መካዚኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? info
التفاسير:

external-link copy
10 : 38

أَمۡ لَهُم مُّلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَاۖ فَلۡيَرۡتَقُواْ فِي ٱلۡأَسۡبَٰبِ

10. ወይስ የሰማይ የምድር እና የመካከላቸዉም ንግስና የእነርሱ ነውን? (ነው ካሉ) እስቲ በመሰላሎች ወደ ላይ ይውጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 38

جُندٞ مَّا هُنَالِكَ مَهۡزُومٞ مِّنَ ٱلۡأَحۡزَابِ

11. እነርሱም እዚያ ዘንድ ከአህዛብ ሁሉ ተሸናፊ የሆነ ሰራዊት ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 38

كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَعَادٞ وَفِرۡعَوۡنُ ذُو ٱلۡأَوۡتَادِ

12. ከእነርሱም በፊት የኑህ ህዝቦች፤ ዓድ እና የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባብለዋል። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 38

وَثَمُودُ وَقَوۡمُ لُوطٖ وَأَصۡحَٰبُ لۡـَٔيۡكَةِۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلۡأَحۡزَابُ

13. ሰሙድም፤ የሉጥ ሰዎችም፤ የአይካ ሰዎችም፤ አስተባበሉ:: እነዚህ አህዛቦቹ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 38

إِن كُلٌّ إِلَّا كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ

14. ሁሉም መልዕክተኞችን ያስዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም:: ከዚያ ቅጣቴ ተረጋገጠባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 38

وَمَا يَنظُرُ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ مَّا لَهَا مِن فَوَاقٖ

15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ ያችን ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲት ጩኸት ብቻ እንጂ ሌላን አይጠባበቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 38

وَقَالُواْ رَبَّنَا عَجِّل لَّنَا قِطَّنَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ

16. (በመሳለቅም) «ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት ቅጣታችንን አጣድፍልን» አሉ። info
التفاسير: