Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
20 : 31

أَلَمۡ تَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَأَسۡبَغَ عَلَيۡكُمۡ نِعَمَهُۥ ظَٰهِرَةٗ وَبَاطِنَةٗۗ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُجَٰدِلُ فِي ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَلَا هُدٗى وَلَا كِتَٰبٖ مُّنِيرٖ

20. (ሰዎች ሆይ!) አላህ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ፤ ጸጋዎችንም ግልጽም ይሁኑ ድብቅ የሞላላችሁ መሆኑን አታዩምን? ከስሞች መካከል ያለ በቂ እውቀትና ያለ መሪ፤ ያለ ግልጽ መጽሀፍም፤ ስለ አላህ የሚከራከር አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 31

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّبِعُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ قَالُواْ بَلۡ نَتَّبِعُ مَا وَجَدۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَآۚ أَوَلَوۡ كَانَ ٱلشَّيۡطَٰنُ يَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ

21. ለእነርሱም «አላህ ያወረደውን ተከተሉ።» በተባሉ ጊዜ «አይደለም በእርሱ ላይ አባቶቻችንን ያገኘንበትን እንከተላለን።» ይላሉ:: ሰይጣን (ይህን ተግባር በማስዋብ) ወደ እሳት ቅጣት የሚጠራቸው ቢሆንም ይከተሏቸዋልን? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 31

۞ وَمَن يُسۡلِمۡ وَجۡهَهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ وَهُوَ مُحۡسِنٞ فَقَدِ ٱسۡتَمۡسَكَ بِٱلۡعُرۡوَةِ ٱلۡوُثۡقَىٰۗ وَإِلَى ٱللَّهِ عَٰقِبَةُ ٱلۡأُمُورِ

22. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥ ሁሉ ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ጨበጠ:: የነገሩ ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 31

وَمَن كَفَرَ فَلَا يَحۡزُنكَ كُفۡرُهُۥٓۚ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ فَنُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ የካደም ሁሉ ክህደቱ አያሳዝንህ። መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነውና:: ከዚያም የሰሩትንም ሁሉ እንነግራቸዋለን:: አላህ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃልና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 31

نُمَتِّعُهُمۡ قَلِيلٗا ثُمَّ نَضۡطَرُّهُمۡ إِلَىٰ عَذَابٍ غَلِيظٖ

24. ጥቂትን ጊዜ እናጣቅማቸዋለን:: ከዚያም ወደ ብርቱ ቅጣት እናስገድዳቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 31

وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۚ قُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

25. ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው።» ይላሉ። «ምስጋና ሁሉ ለአላህ ብቻ ይገባው።» በላቸው:: ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 31

لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ

26. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: አላህ በራሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 31

وَلَوۡ أَنَّمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ مِن شَجَرَةٍ أَقۡلَٰمٞ وَٱلۡبَحۡرُ يَمُدُّهُۥ مِنۢ بَعۡدِهِۦ سَبۡعَةُ أَبۡحُرٖ مَّا نَفِدَتۡ كَلِمَٰتُ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

27. በምድር ያሉ ሁሉ ዛፎች ብዕሮች ቢሆኑ ኖሮ ባህሩም ከእርሱ ማለቅ በኋላ ሰባት ባህሮች የሚጨመሩለት ሆኖ ቀለም ቢሆንና ቢጻፍባቸው የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 31

مَّا خَلۡقُكُمۡ وَلَا بَعۡثُكُمۡ إِلَّا كَنَفۡسٖ وَٰحِدَةٍۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٌ

28. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን መፍጠርና እናንተን መቀስቀስ እንደ አንዲት ነፍስ እንጂ ሌላ አይደለም:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነውና:: info
التفاسير: