Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

አል ፉርቃን

external-link copy
1 : 25

تَبَارَكَ ٱلَّذِي نَزَّلَ ٱلۡفُرۡقَانَ عَلَىٰ عَبۡدِهِۦ لِيَكُونَ لِلۡعَٰلَمِينَ نَذِيرًا

1. ያ ፉርቃንን (እውነትን ከውሸት የሚለየውን) ቁርኣን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብሩ ላቀ (ጥራት ተገባው)። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 25

ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَمۡ يَتَّخِذۡ وَلَدٗا وَلَمۡ يَكُن لَّهُۥ شَرِيكٞ فِي ٱلۡمُلۡكِ وَخَلَقَ كُلَّ شَيۡءٖ فَقَدَّرَهُۥ تَقۡدِيرٗا

2. አላህ ያ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ የሆነ፤ ልጅንም ያልያዘ (ልጅም የሌለው)፤ በንግስናዉም ተጋሪ የሌለው፤ ሁሉንም ነገር የፈጠረና በትክክልም (በስርአት) የመጠነው አምላክ ነው። info
التفاسير: