Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
15 : 16

وَأَلۡقَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِكُمۡ وَأَنۡهَٰرٗا وَسُبُلٗا لَّعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ

15. በምድር ውስጥ በናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት። ትመሩም ዘንድ ጅረቶችንና መንገዶችን አደረገ። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 16

وَعَلَٰمَٰتٖۚ وَبِٱلنَّجۡمِ هُمۡ يَهۡتَدُونَ

16. ምልክቶችንም አደረገ:: በከዋክብትም እነርሱ ይመራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 16

أَفَمَن يَخۡلُقُ كَمَن لَّا يَخۡلُقُۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

17. (ሰዎች ሆይ!) የሚፈጥር ልክ እንደማይፈጥር ነውን? አትገሠጹምን? info
التفاسير:

external-link copy
18 : 16

وَإِن تَعُدُّواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحۡصُوهَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ

18. የአላህን ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም:: አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 16

وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعۡلِنُونَ

19. አላህ የምትደብቁትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ያውቃል:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 16

وَٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَخۡلُقُونَ شَيۡـٔٗا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ

20. እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው አማልክት ሁሉ ምንንም አይፈጥሩም:: እንዲያዉም እነርሱ ራሳቸው ይፈጠራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 16

أَمۡوَٰتٌ غَيۡرُ أَحۡيَآءٖۖ وَمَا يَشۡعُرُونَ أَيَّانَ يُبۡعَثُونَ

21. እነርሱ ሕያው ያልሆኑ ሙታን ናቸው:: እራሳቸው እንኳን መቼ እንደሚቀሰቀሱ አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 16

إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۚ فَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ قُلُوبُهُم مُّنكِرَةٞ وَهُم مُّسۡتَكۡبِرُونَ

22. አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲያን ናቸው:: እነርሱም የኮሩ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 16

لَا جَرَمَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡتَكۡبِرِينَ

23. አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለበትም:: እርሱ ኩሩዎችን አይወድም:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 16

وَإِذَا قِيلَ لَهُم مَّاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمۡ قَالُوٓاْ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

24. ጌታችሁ በሙሐመድ ላይ ምን አወረደ በተባሉ ጊዜም: «የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶችን ነው።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 16

لِيَحۡمِلُوٓاْ أَوۡزَارَهُمۡ كَامِلَةٗ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَمِنۡ أَوۡزَارِ ٱلَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيۡرِ عِلۡمٍۗ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ

25. ይህንን የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉና ከነዚያም ያለ ዕውቀት ሆነው ከሚያጣምሟቸው ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው:: ንቁ የሚሸከሙት ኃጢአት ምንኛ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
26 : 16

قَدۡ مَكَرَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَأَتَى ٱللَّهُ بُنۡيَٰنَهُم مِّنَ ٱلۡقَوَاعِدِ فَخَرَّ عَلَيۡهِمُ ٱلسَّقۡفُ مِن فَوۡقِهِمۡ وَأَتَىٰهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ

26. እነዚያ ከእነርሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት ከሓዲያን አሴሩ:: ከዚያም አላህ ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ:: እናም ጣሪያው በላያቸው ላይ ወደቀባቸው:: ቅጣቱም ከማያውቁት ስፍራ መጣባቸው:: info
التفاسير: