Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Akademie Afrika

Nummer der Seite:close

external-link copy
52 : 15

إِذۡ دَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَقَالُواْ سَلَٰمٗا قَالَ إِنَّا مِنكُمۡ وَجِلُونَ

52. በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: እርሱም፡- «እኛ ከናንተ ፈሪዎች ነን።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
53 : 15

قَالُواْ لَا تَوۡجَلۡ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٖ

53. «አትፍራ እኛ አዋቂ በሆነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
54 : 15

قَالَ أَبَشَّرۡتُمُونِي عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِيَ ٱلۡكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ

54. «እርጅና የደረሰብኝ ከመሆኔ ጋር አበሰራችሁኝን? በምን ታበስሩኛላችሁ?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
55 : 15

قَالُواْ بَشَّرۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡقَٰنِطِينَ

55. «በእውነት አበሰርንህ ከተስፋ ቆራጮችም አትሁን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
56 : 15

قَالَ وَمَن يَقۡنَطُ مِن رَّحۡمَةِ رَبِّهِۦٓ إِلَّا ٱلضَّآلُّونَ

56. «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
57 : 15

قَالَ فَمَا خَطۡبُكُمۡ أَيُّهَا ٱلۡمُرۡسَلُونَ

57. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ኧረ ለመሆኑ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
58 : 15

قَالُوٓاْ إِنَّآ أُرۡسِلۡنَآ إِلَىٰ قَوۡمٖ مُّجۡرِمِينَ

58. አሉም: «እኛ አመፀኞች ወደ ሆኑ ሕዝቦች ተልከናል። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 15

إِلَّآ ءَالَ لُوطٍ إِنَّا لَمُنَجُّوهُمۡ أَجۡمَعِينَ

59. «የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን። info
التفاسير:

external-link copy
60 : 15

إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ قَدَّرۡنَآ إِنَّهَا لَمِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ

60. «ሚስቱ ብቻ ስትቀር።» (አሉ) እርሷንማ በቅጣቱ ውስጥ ከሚቀሩት ሰዎች መሆኗን ወስነናል። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 15

فَلَمَّا جَآءَ ءَالَ لُوطٍ ٱلۡمُرۡسَلُونَ

61. መልዕክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ። info
التفاسير:

external-link copy
62 : 15

قَالَ إِنَّكُمۡ قَوۡمٞ مُّنكَرُونَ

62. ሉጥ «እናንተ የተሳሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
63 : 15

قَالُواْ بَلۡ جِئۡنَٰكَ بِمَا كَانُواْ فِيهِ يَمۡتَرُونَ

63. አሉም: «አይደለም:: እኛ ህዝቦችህ በእሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንልህ። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 15

وَأَتَيۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ

64. «እውነትንም ይዘን መጣንልህ:: እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን። info
التفاسير:

external-link copy
65 : 15

فَأَسۡرِ بِأَهۡلِكَ بِقِطۡعٖ مِّنَ ٱلَّيۡلِ وَٱتَّبِعۡ أَدۡبَٰرَهُمۡ وَلَا يَلۡتَفِتۡ مِنكُمۡ أَحَدٞ وَٱمۡضُواْ حَيۡثُ تُؤۡمَرُونَ

65. «ከቤተሰብህ ጋር በሌሊቱ ከፊል (አጋማሽ) ላይ ሂድ:: በኋላቸዉም ተከተል:: ከናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉ።» አሉት:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 15

وَقَضَيۡنَآ إِلَيۡهِ ذَٰلِكَ ٱلۡأَمۡرَ أَنَّ دَابِرَ هَٰٓؤُلَآءِ مَقۡطُوعٞ مُّصۡبِحِينَ

66. ወደ እርሱም ያንን ትዕዛዝ አወረድን :: እርሱም የእነዚህ ሕዝቦች መጨረሻ ያነጉ ሲሆኑ ስራቸው መቆረጥ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 15

وَجَآءَ أَهۡلُ ٱلۡمَدِينَةِ يَسۡتَبۡشِرُونَ

67. የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ሆነው መጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 15

قَالَ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ ضَيۡفِي فَلَا تَفۡضَحُونِ

68. ሉጥም አለ፡- «እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ። info
التفاسير:

external-link copy
69 : 15

وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُخۡزُونِ

69. «አላህንም ፍሩ አታሳፍሩኝም።» info
التفاسير:

external-link copy
70 : 15

قَالُوٓاْ أَوَلَمۡ نَنۡهَكَ عَنِ ٱلۡعَٰلَمِينَ

70. «ከዓለማት ማንንም እንዳታስተናግድ አልከለከልንህምን?» አሉት። info
التفاسير: