Übersetzung der Bedeutungen von dem heiligen Quran - Amharische Übersetzung - Muhammad Sadiq

Nummer der Seite:close

external-link copy
17 : 68

إِنَّا بَلَوۡنَٰهُمۡ كَمَا بَلَوۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ إِذۡ أَقۡسَمُواْ لَيَصۡرِمُنَّهَا مُصۡبِحِينَ

እኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 68

وَلَا يَسۡتَثۡنُونَ

(በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 68

فَطَافَ عَلَيۡهَا طَآئِفٞ مِّن رَّبِّكَ وَهُمۡ نَآئِمُونَ

እነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 68

فَأَصۡبَحَتۡ كَٱلصَّرِيمِ

እንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 68

فَتَنَادَوۡاْ مُصۡبِحِينَ

ያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 68

أَنِ ٱغۡدُواْ عَلَىٰ حَرۡثِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰرِمِينَ

«ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱ» በማለት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 68

فَٱنطَلَقُواْ وَهُمۡ يَتَخَٰفَتُونَ

እነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 68

أَن لَّا يَدۡخُلَنَّهَا ٱلۡيَوۡمَ عَلَيۡكُم مِّسۡكِينٞ

ዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 68

وَغَدَوۡاْ عَلَىٰ حَرۡدٖ قَٰدِرِينَ

(ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 68

فَلَمَّا رَأَوۡهَا قَالُوٓاْ إِنَّا لَضَآلُّونَ

(ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 68

بَلۡ نَحۡنُ مَحۡرُومُونَ

«ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነን» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 68

قَالَ أَوۡسَطُهُمۡ أَلَمۡ أَقُل لَّكُمۡ لَوۡلَا تُسَبِّحُونَ

ትክክለኛቸው «ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 68

قَالُواْ سُبۡحَٰنَ رَبِّنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

«ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 68

فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَلَٰوَمُونَ

የሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 68

قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا طَٰغِينَ

«ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 68

عَسَىٰ رَبُّنَآ أَن يُبۡدِلَنَا خَيۡرٗا مِّنۡهَآ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا رَٰغِبُونَ

«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤» (አሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 68

كَذَٰلِكَ ٱلۡعَذَابُۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ

ቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 68

إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمۡ جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ

ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 68

أَفَنَجۡعَلُ ٱلۡمُسۡلِمِينَ كَٱلۡمُجۡرِمِينَ

ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን? info
التفاسير:

external-link copy
36 : 68

مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ

ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 68

أَمۡ لَكُمۡ كِتَٰبٞ فِيهِ تَدۡرُسُونَ

በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 68

إِنَّ لَكُمۡ فِيهِ لَمَا تَخَيَّرُونَ

በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል) info
التفاسير:

external-link copy
39 : 68

أَمۡ لَكُمۡ أَيۡمَٰنٌ عَلَيۡنَا بَٰلِغَةٌ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ إِنَّ لَكُمۡ لَمَا تَحۡكُمُونَ

ወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
40 : 68

سَلۡهُمۡ أَيُّهُم بِذَٰلِكَ زَعِيمٌ

በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 68

أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَآءُ فَلۡيَأۡتُواْ بِشُرَكَآئِهِمۡ إِن كَانُواْ صَٰدِقِينَ

ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) «ተጋሪዎች» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ «ተጋሪዎቻቸውን» ያምጡ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 68

يَوۡمَ يُكۡشَفُ عَن سَاقٖ وَيُدۡعَوۡنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ

ባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡ info
التفاسير: