Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

Broj stranice:close

external-link copy
58 : 7

وَٱلۡبَلَدُ ٱلطَّيِّبُ يَخۡرُجُ نَبَاتُهُۥ بِإِذۡنِ رَبِّهِۦۖ وَٱلَّذِي خَبُثَ لَا يَخۡرُجُ إِلَّا نَكِدٗاۚ كَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَشۡكُرُونَ

58. መልካሙ አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ ያማረ ሆኖ ይወጣል። ያ መጥፎ የሆነው አገር ደግሞ በቃዩ ደካማ ሆኖ እንጂ አይወጣም:: ልክ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ህዝቦች ተዓምራትን እናብራራለን። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 7

لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

59. ኑሕን ወደ ወገኖቹ ላክነው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
60 : 7

قَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

60. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹ «እኛ በግልጽ ስህተት ውስጥ ሆነህ እናይሀለን።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 7

قَالَ يَٰقَوۡمِ لَيۡسَ بِي ضَلَٰلَةٞ وَلَٰكِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

61. ኑሕም አለ: «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም። ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልዕክተኛ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
62 : 7

أُبَلِّغُكُمۡ رِسَٰلَٰتِ رَبِّي وَأَنصَحُ لَكُمۡ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ

62. «የጌታዬን መልዕክቶች አደርስላችኋለሁ:: ለናንተም እመክራችኋለሁ:: ከአላህ በኩልም የማታውቁትን አውቃለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 7

أَوَعَجِبۡتُمۡ أَن جَآءَكُمۡ ذِكۡرٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَلَىٰ رَجُلٖ مِّنكُمۡ لِيُنذِرَكُمۡ وَلِتَتَّقُواْ وَلَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ

63. «አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከናንተው ጎሳ መካከል በሆነ ሰው ላይ እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ስለመጣላችሁ ትደነቃላችሁን?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
64 : 7

فَكَذَّبُوهُ فَأَنجَيۡنَٰهُ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَأَغۡرَقۡنَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمًا عَمِينَ

64. ወዲያዉም አስተባበሉት:: እርሱንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያሉትንም በታንኳዋ ውስጥ አዳንናቸው:: እነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን ግን በባህር አሰመጥናቸው:: እነርሱ ልበ እውራን ህዝቦች ነበሩና:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 7

۞ وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمۡ هُودٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ

65. ወደ ዓድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሁድን ላክን። «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: የአላህን ቅጣት አትፈሩምን?» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
66 : 7

قَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦٓ إِنَّا لَنَرَىٰكَ فِي سَفَاهَةٖ وَإِنَّا لَنَظُنُّكَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

66. ከህዝቦቹ መካከል መሪዎቹም «እኛ በሞኝነት ላይ ሆነህ እናይሀለን:: እኛ ከውሸተኞቹ ነህ ብለንም እንጠረጥርሀለን።» አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
67 : 7

قَالَ يَٰقَوۡمِ لَيۡسَ بِي سَفَاهَةٞ وَلَٰكِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

67. እርሱም አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም:: ግን እኔ ከአለማት ጌታ የተላኩ ነኝ። info
التفاسير: