Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

አል ቀለም

external-link copy
1 : 68

نٓۚ وَٱلۡقَلَمِ وَمَا يَسۡطُرُونَ

1. ኑን፤ በብዕር እና በዚያም በሱ በሚጽፉት ሁሉ እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 68

مَآ أَنتَ بِنِعۡمَةِ رَبِّكَ بِمَجۡنُونٖ

2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ በጌታህ ጸጋ ምክኒያት ዕብድ አይደለህም:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 68

وَإِنَّ لَكَ لَأَجۡرًا غَيۡرَ مَمۡنُونٖ

3. ላንተም ከጌታህ የማይቋረጥ ምንዳ (የልፋት ዋጋ) በእርግጥ አለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 68

وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٖ

4. አንተም በታላቅ ጸባይ ላይ ነህ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 68

فَسَتُبۡصِرُ وَيُبۡصِرُونَ

5. ወደ ፊት አንተም ታያለህ፤ እነርሱም ያያሉ፤ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 68

بِأَييِّكُمُ ٱلۡمَفۡتُونُ

6. ዕብደት በማንኛችሁ እንዳለ (እብዱ ማን እንደሆነ):: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 68

إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ

7. ጌታህ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው። ወደ ቀናው መንገድ ተመሪዎችንም አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 68

فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِينَ

8. ስለዚህ ለአስተባባዩች (ሁሉ) አትታዘዝ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 68

وَدُّواْ لَوۡ تُدۡهِنُ فَيُدۡهِنُونَ

9. (አስተባባዩች) ብትመሳሰላቸውና እነርሱም ቢመሳሰሉህ ተመኙ:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 68

وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافٖ مَّهِينٍ

10. መሓለኛን ወራዳን ሁሉ አትታዘዝ። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 68

هَمَّازٖ مَّشَّآءِۭ بِنَمِيمٖ

11. ሰውን አነዋሪን፤ ነገር አሳባቂን፤ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 68

مَّنَّاعٖ لِّلۡخَيۡرِ مُعۡتَدٍ أَثِيمٍ

12.ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፤ ወሰን አላፊን፤ ኃጢአተኛንም፤ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 68

عُتُلِّۭ بَعۡدَ ذَٰلِكَ زَنِيمٍ

13. ልበ ደረቅን ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የዝሙት ልጅ ዲቃላን (አትታዘዝ):: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 68

أَن كَانَ ذَا مَالٖ وَبَنِينَ

14. የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመሆኑ (ያስተባብላል)። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 68

إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا قَالَ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ

15. በእርሱ ላይ እንቀፆቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 68

سَنَسِمُهُۥ عَلَى ٱلۡخُرۡطُومِ

16. በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክትን እናደርግበታለን:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 68

إِنَّا بَلَوۡنَٰهُمۡ كَمَا بَلَوۡنَآ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ إِذۡ أَقۡسَمُواْ لَيَصۡرِمُنَّهَا مُصۡبِحِينَ

17. እኛ እነዚያን የአትክልቲቱን ባለቤቶች ማልደው ፍሬዋን ሊለቅሟት (አላህ ቢሻ ሳይሉ) በማሉ ጊዜ እንደሞከርን ሁሉ የመካ ሰዎችንም ሞከርናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 68

وَلَا يَسۡتَثۡنُونَ

18. (በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 68

فَطَافَ عَلَيۡهَا طَآئِفٞ مِّن رَّبِّكَ وَهُمۡ نَآئِمُونَ

19.እነርሱ የተኙ ሆነዉም ሳሉ ከጌታህ የሆነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 68

فَأَصۡبَحَتۡ كَٱلصَّرِيمِ

20. እንደ ሌሊት ጨለማ የከሰለች ሆና አነጋች (አደረች)። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 68

فَتَنَادَوۡاْ مُصۡبِحِينَ

21.ያነጉም ሆነው ተጠራሩ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 68

أَنِ ٱغۡدُواْ عَلَىٰ حَرۡثِكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰرِمِينَ

22. "ቆራጮች እንደ ሆናችሁ ወደ እርሻችሁ ለመሄድ ማልዱ በማለት" (ተጠራሩ):: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 68

فَٱنطَلَقُواْ وَهُمۡ يَتَخَٰفَتُونَ

23. እነርሱ የሚያሾካሾኩ ሆነው ሄዱም:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 68

أَن لَّا يَدۡخُلَنَّهَا ٱلۡيَوۡمَ عَلَيۡكُم مِّسۡكِينٞ

24. ዛሬ በእናንተ ላይ አንድም ድሃ እንዳይገባት በማለትና info
التفاسير:

external-link copy
25 : 68

وَغَدَوۡاْ عَلَىٰ حَرۡدٖ قَٰدِرِينَ

25. ድሆችን በመከልከልም ላይ በሀሳባቸው ቻዮች ሆነው ማለዱ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 68

فَلَمَّا رَأَوۡهَا قَالُوٓاْ إِنَّا لَضَآلُّونَ

26. ከዚያ ተቃጥላ ባዩዋት ጊዜ (እንዲህ) አሉ: «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን፤ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 68

بَلۡ نَحۡنُ مَحۡرُومُونَ

27. «ይልቁንም እኛ ከአላህ የተከለከልን እደለ ቢሶች ነን» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 68

قَالَ أَوۡسَطُهُمۡ أَلَمۡ أَقُل لَّكُمۡ لَوۡلَا تُسَبِّحُونَ

28. (ከመካከላቸው) ትክክለኛቸው (አስተዋያቸው)፡- «እናንተ አላህን ለምን አታጠሩም (አታወሱም) አላልኳችሁም ነበርን?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 68

قَالُواْ سُبۡحَٰنَ رَبِّنَآ إِنَّا كُنَّا ظَٰلِمِينَ

29. «(ሁላቸዉም) ጌታችን ጥራት ይገባው፤ እኛ በዳዩች ነበርን» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 68

فَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَلَٰوَمُونَ

30. እርስ በራሳቸው የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 68

قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَآ إِنَّا كُنَّا طَٰغِينَ

31. «ዋ፤ጥፋታችን፤ እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 68

عَسَىٰ رَبُّنَآ أَن يُبۡدِلَنَا خَيۡرٗا مِّنۡهَآ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا رَٰغِبُونَ

32. «ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል:: እኛ ወደ ጌታችን ከጃዩች ነን» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 68

كَذَٰلِكَ ٱلۡعَذَابُۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ

33. (የአላህ) ቅጣቱ ልክ እንደዚሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ከዚህ የበለጠ ከባድ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ (ከዚህ ቅጣት በተጠነቀቁ ነበር):: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 68

إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمۡ جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ

34. ለጥንቁቆች በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 68

أَفَنَجۡعَلُ ٱلۡمُسۡلِمِينَ كَٱلۡمُجۡرِمِينَ

35. ሙስሊሞችን እንደ ከሓዲያን እናደርጋለን? (አናደርግም):: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 68

مَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ

36. ለእናንተ ምን (አስረጂ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ( ምን ነካችሁ):: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 68

أَمۡ لَكُمۡ كِتَٰبٞ فِيهِ تَدۡرُسُونَ

37. በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 68

إِنَّ لَكُمۡ فِيهِ لَمَا تَخَيَّرُونَ

38. በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁን? (የሚል):: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 68

أَمۡ لَكُمۡ أَيۡمَٰنٌ عَلَيۡنَا بَٰلِغَةٌ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ إِنَّ لَكُمۡ لَمَا تَحۡكُمُونَ

39. ወይስ «ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ» በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሳኤ ቀን ደራሽ የሆኑ መሐላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
40 : 68

سَلۡهُمۡ أَيُّهُم بِذَٰلِكَ زَعِيمٌ

40. በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 68

أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَآءُ فَلۡيَأۡتُواْ بِشُرَكَآئِهِمۡ إِن كَانُواْ صَٰدِقِينَ

41. ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) ተጋሪዎች አሏቸውን? እውነተኞችም እንደሆኑ ተጋሪዎቻቸውን ያምጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 68

يَوۡمَ يُكۡشَفُ عَن سَاقٖ وَيُدۡعَوۡنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያን ባት የሚገለጥበትን፤ (ከሓዲያን) ወደ መስገድ የሚጠሩበትና የማይችሉበትን ቀን (አስታውስ):: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 68

خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۖ وَقَدۡ كَانُواْ يُدۡعَوۡنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ وَهُمۡ سَٰلِمُونَ

43. ዓይኖቻቸው የፈሩ፤ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲሆኑ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን):: እነርሱ (በምድረ ዓለም) ደህና ሆነው ሳሉ ወደ ስግድት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 68

فَذَرۡنِي وَمَن يُكَذِّبُ بِهَٰذَا ٱلۡحَدِيثِۖ سَنَسۡتَدۡرِجُهُم مِّنۡ حَيۡثُ لَا يَعۡلَمُونَ

44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመሆኑም እኔን በዚህ ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተወኝ፤ (ለእነርሱ እኔ እበቃሃለሁ):: ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 68

وَأُمۡلِي لَهُمۡۚ إِنَّ كَيۡدِي مَتِينٌ

45. እነርሱንም አዘገያቸዋለሁ:: (ዘዴዬ) ብቀላየ ብርቱ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 68

أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ أَجۡرٗا فَهُم مِّن مَّغۡرَمٖ مُّثۡقَلُونَ

46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይንስ በእውነቱ (በማስተማርህ) ዋጋን እንዲከፍሉህ ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን? info
التفاسير:

external-link copy
47 : 68

أَمۡ عِندَهُمُ ٱلۡغَيۡبُ فَهُمۡ يَكۡتُبُونَ

47. ወይስ ከእነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር እውቀት አለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን? info
التفاسير:

external-link copy
48 : 68

فَٱصۡبِرۡ لِحُكۡمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ ٱلۡحُوتِ إِذۡ نَادَىٰ وَهُوَ مَكۡظُومٞ

48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ ለጌታህ (ዉሳኔ) ፍርድ ታገስ:: (በመበሳጨትና ባለ መታገስ) እንደ ዓሳው ባለቤት እንደ (ነብዩ ዩኑስ) አትሁን:: እርሱ በጭንቀት የተሞላ ሆኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ info
التفاسير:

external-link copy
49 : 68

لَّوۡلَآ أَن تَدَٰرَكَهُۥ نِعۡمَةٞ مِّن رَّبِّهِۦ لَنُبِذَ بِٱلۡعَرَآءِ وَهُوَ مَذۡمُومٞ

49. ከጌታው የሆነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ሆኖ በተጣለ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 68

فَٱجۡتَبَٰهُ رَبُّهُۥ فَجَعَلَهُۥ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

50. ጌታዉም (በነብይነት) መረጠው:: ከደጋጎችም አደረገው:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 68

وَإِن يَكَادُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَيُزۡلِقُونَكَ بِأَبۡصَٰرِهِمۡ لَمَّا سَمِعُواْ ٱلذِّكۡرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُۥ لَمَجۡنُونٞ

51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነሆ እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ «እርሱም በእርግጥ እብድ ነዉም» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 68

وَمَا هُوَ إِلَّا ذِكۡرٞ لِّلۡعَٰلَمِينَ

52.እርሱ ግን ለዓለማት መገሰጫ (ገሳጭ) እንጂ ሌላ አይደለም:: info
التفاسير: