Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

አጥ ጡር

external-link copy
1 : 52

وَٱلطُّورِ

1. በጡር (ጋራ)፤ እምላለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 52

وَكِتَٰبٖ مَّسۡطُورٖ

2. በተጻፈው መጽሓፍም፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 52

فِي رَقّٖ مَّنشُورٖ

3. በተዘረጋው ብራና ላይ፤ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 52

وَٱلۡبَيۡتِ ٱلۡمَعۡمُورِ

4. በደመቀው ቤትም፤ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 52

وَٱلسَّقۡفِ ٱلۡمَرۡفُوعِ

5. ከፍ በተደረገው ጣራም፤ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 52

وَٱلۡبَحۡرِ ٱلۡمَسۡجُورِ

6. በእሳት በተሞላው ባህርም እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 52

إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ لَوَٰقِعٞ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት በእርግጥ ወዳቂ ነው (የማይቀር ነው):: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 52

مَّا لَهُۥ مِن دَافِعٖ

8. ለእርሱ ምንም ገፍታሪ የለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 52

يَوۡمَ تَمُورُ ٱلسَّمَآءُ مَوۡرٗا

9. ሰማይ ብርቱ መዞርን በምትዞርበት ቀን (ይሆናል):: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 52

وَتَسِيرُ ٱلۡجِبَالُ سَيۡرٗا

10. ተራራዎችም መሄድን በሚሄዱበት ቀን:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 52

فَوَيۡلٞ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُكَذِّبِينَ

11. ላስተባባዮችም ሁሉ ያን ጊዜ ወዮላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 52

ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي خَوۡضٖ يَلۡعَبُونَ

12. ለነዚያ ለእነርሱ በውሸት ውስጥ የሚጫወቱ ለሆኑት ሰዎች:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 52

يَوۡمَ يُدَعُّونَ إِلَىٰ نَارِ جَهَنَّمَ دَعًّا

13. ወደ ገሀነም እሳት በሀይል መገፍተርን በሚገፈተሩበት ቀን info
التفاسير:

external-link copy
14 : 52

هَٰذِهِ ٱلنَّارُ ٱلَّتِي كُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ

14. «ይህች ያቺ በእርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት ይባላሉ»። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 52

أَفَسِحۡرٌ هَٰذَآ أَمۡ أَنتُمۡ لَا تُبۡصِرُونَ

15. «ይህ (ፊት ትሉን እንደነበራችሁት) ድግምት ነውን? ወይስ እናንተ አታዩምን? info
التفاسير:

external-link copy
16 : 52

ٱصۡلَوۡهَا فَٱصۡبِرُوٓاْ أَوۡ لَا تَصۡبِرُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡكُمۡۖ إِنَّمَا تُجۡزَوۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

16. «ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሱ በእናንተ ላይ እኩል ነው:: የምትመነዱት ትሰሩት የነበራችሁትን ፍዳ ብቻ ነው» ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 52

إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَنَعِيمٖ

17. አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 52

فَٰكِهِينَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡ وَوَقَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡ عَذَابَ ٱلۡجَحِيمِ

18. ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ሆነው በገነት ውስጥ ናቸው:: የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 52

كُلُواْ وَٱشۡرَبُواْ هَنِيٓـَٔۢا بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

19. «ትሰሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ሆናችሁ ብሉ ጠጡም» (ይባላሉ።) info
التفاسير:

external-link copy
20 : 52

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ سُرُرٖ مَّصۡفُوفَةٖۖ وَزَوَّجۡنَٰهُم بِحُورٍ عِينٖ

20. በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ሆነው በገነት ይኖራሉ:: አይናማዎች በሆኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 52

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱتَّبَعَتۡهُمۡ ذُرِّيَّتُهُم بِإِيمَٰنٍ أَلۡحَقۡنَا بِهِمۡ ذُرِّيَّتَهُمۡ وَمَآ أَلَتۡنَٰهُم مِّنۡ عَمَلِهِم مِّن شَيۡءٖۚ كُلُّ ٱمۡرِيِٕۭ بِمَا كَسَبَ رَهِينٞ

21. እነዚያም በአላህ ያመኑና ዝርያቸዉም በእውነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን ከእነርሱ ጋር እናስጠጋቸዋለን:: ከስራዎቻቸዉም ምንንም አናጎድልባቸዉም:: ሰው ሁሉ በሰራው ስራ ተጠያቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 52

وَأَمۡدَدۡنَٰهُم بِفَٰكِهَةٖ وَلَحۡمٖ مِّمَّا يَشۡتَهُونَ

22. ከሚሹትም ሁሉ እሸትንና ስጋን እንጨምርላቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 52

يَتَنَٰزَعُونَ فِيهَا كَأۡسٗا لَّا لَغۡوٞ فِيهَا وَلَا تَأۡثِيمٞ

23. በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ:: በውስጧ ውድቅ ንግግርና መወንጀልም የለም:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 52

۞ وَيَطُوفُ عَلَيۡهِمۡ غِلۡمَانٞ لَّهُمۡ كَأَنَّهُمۡ لُؤۡلُؤٞ مَّكۡنُونٞ

24. ለእነርሱም የሆኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሰላፍ ይዘዋወራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 52

وَأَقۡبَلَ بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ يَتَسَآءَلُونَ

25. የሚጠያየቁ ሆነዉም ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይዞራል:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 52

قَالُوٓاْ إِنَّا كُنَّا قَبۡلُ فِيٓ أَهۡلِنَا مُشۡفِقِينَ

26. ይላሉም: «እኛ ፊት በቤተሰቦቻችን ውስጥ ከቅጣት ፈሪዎች ነበርን። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 52

فَمَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡنَا وَوَقَىٰنَا عَذَابَ ٱلسَّمُومِ

27. «አላህ በእኛ ላይ ለገሰ:: የመርዛም እሳት ቅጣትንም ጠበቀን:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 52

إِنَّا كُنَّا مِن قَبۡلُ نَدۡعُوهُۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡبَرُّ ٱلرَّحِيمُ

28. «እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበርን:: እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 52

فَذَكِّرۡ فَمَآ أَنتَ بِنِعۡمَتِ رَبِّكَ بِكَاهِنٖ وَلَا مَجۡنُونٍ

29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ሰዎችን) አስታውስ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም እብድም አይደለህም:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 52

أَمۡ يَقُولُونَ شَاعِرٞ نَّتَرَبَّصُ بِهِۦ رَيۡبَ ٱلۡمَنُونِ

30. «ይልቁንም የሞትን አደጋ በእርሱ የምንጠባበቅበት የሆነ ባለ ቅኔ ነው» ይላሉን? info
التفاسير:

external-link copy
31 : 52

قُلۡ تَرَبَّصُواْ فَإِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُتَرَبِّصِينَ

31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ተጠባበቁ እኔም ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 52

أَمۡ تَأۡمُرُهُمۡ أَحۡلَٰمُهُم بِهَٰذَآۚ أَمۡ هُمۡ قَوۡمٞ طَاغُونَ

32. አእምሮዎቻቸው በዚህ ተግባር ያዟቸዋልን? ወይስ በእውነቱ እነርሱ ወሰን አላፊ ህዝቦች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 52

أَمۡ يَقُولُونَ تَقَوَّلَهُۥۚ بَل لَّا يُؤۡمِنُونَ

33. ወይም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም። ይልቁንም አያምኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 52

فَلۡيَأۡتُواْ بِحَدِيثٖ مِّثۡلِهِۦٓ إِن كَانُواْ صَٰدِقِينَ

34. እውነተኞችም ከሆኑ መሰሉ የሆነን ንግግር ያምጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 52

أَمۡ خُلِقُواْ مِنۡ غَيۡرِ شَيۡءٍ أَمۡ هُمُ ٱلۡخَٰلِقُونَ

35. ወይስ ያለ አንዳች ፈጣሪ ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? info
التفاسير:

external-link copy
36 : 52

أَمۡ خَلَقُواْ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَۚ بَل لَّا يُوقِنُونَ

36. ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም፤ አያረጋግጡም:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 52

أَمۡ عِندَهُمۡ خَزَآئِنُ رَبِّكَ أَمۡ هُمُ ٱلۡمُصَۜيۡطِرُونَ

37. ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸው? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 52

أَمۡ لَهُمۡ سُلَّمٞ يَسۡتَمِعُونَ فِيهِۖ فَلۡيَأۡتِ مُسۡتَمِعُهُم بِسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ

38. ወይስ ለእነርሱ በእርሱ ላይ ከሰማይ የሚያዳምጡበት መሰላል አላቸውን? (እንግዲያውስ) አድማጫቸዉ ሰማሁ የሚለውን ግልጽ አስረጂ ያምጣ:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 52

أَمۡ لَهُ ٱلۡبَنَٰتُ وَلَكُمُ ٱلۡبَنُونَ

39. ወይስ ለእናንተ ወንዶች ልጆች እያሏችሁ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? info
التفاسير:

external-link copy
40 : 52

أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ أَجۡرٗا فَهُم مِّن مَّغۡرَمٖ مُّثۡقَلُونَ

40. ወይስ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? በዚህም እነርሱ በእዳው የተከበዱ ናቸውን? info
التفاسير:

external-link copy
41 : 52

أَمۡ عِندَهُمُ ٱلۡغَيۡبُ فَهُمۡ يَكۡتُبُونَ

41. ወይስ ሩቁ ሚስጢር እነርሱ ዘንድ በመሆኑ እነርሱ ይጽፋሉን? info
التفاسير:

external-link copy
42 : 52

أَمۡ يُرِيدُونَ كَيۡدٗاۖ فَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ هُمُ ٱلۡمَكِيدُونَ

42. ወይስ ተንኮልን (ባንተ) ይሻሉን? እነዚያም የካዱት የተተነኮለባቸው ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 52

أَمۡ لَهُمۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

43. ወይስ ለእነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ አላቸውን? አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 52

وَإِن يَرَوۡاْ كِسۡفٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ سَاقِطٗا يَقُولُواْ سَحَابٞ مَّرۡكُومٞ

44. ከሰማይም ቁራጭን በእነርሱ ላይ ወዳቂ ሆኖ ቢያዩ ኖሮ «ይህ የተደራረበ ደመና ነው» ይሉ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 52

فَذَرۡهُمۡ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي فِيهِ يُصۡعَقُونَ

45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)ያንንም በእርሱ የሚገደሉበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 52

يَوۡمَ لَا يُغۡنِي عَنۡهُمۡ كَيۡدُهُمۡ شَيۡـٔٗا وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ

46. ተንኮላቸው ከእነርሱ ምንም የማይጠቅማቸውንና እነርሱም የማይረዱበትን ቀን እስከሚያገኙ ተዋቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 52

وَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ عَذَابٗا دُونَ ذَٰلِكَ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

47. ለእነዚያም ለበደሉትም ከዚህ ሌላ ቅርብ ቅጣት አለባቸው:: ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 52

وَٱصۡبِرۡ لِحُكۡمِ رَبِّكَ فَإِنَّكَ بِأَعۡيُنِنَاۖ وَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ حِينَ تَقُومُ

48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለጌታህ ፍርድም ታገስ:: አንተ በጥበቃችን ስር ነህና:: ጌታህንም በምትቆም ጊዜ ከማመስገን ጋር አጥራው:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 52

وَمِنَ ٱلَّيۡلِ فَسَبِّحۡهُ وَإِدۡبَٰرَ ٱلنُّجُومِ

49. ከሌሊቱና በከዋክብት መደበቂያም ጊዜ (ንጋት ላይም) አጥራው:: info
التفاسير: