Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

Broj stranice:close

external-link copy
32 : 34

قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ لِلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُوٓاْ أَنَحۡنُ صَدَدۡنَٰكُمۡ عَنِ ٱلۡهُدَىٰ بَعۡدَ إِذۡ جَآءَكُمۖ بَلۡ كُنتُم مُّجۡرِمِينَ

32. እነዚያ የኮሩት ለእነዚያ ለተዋረዱት «ትክክለኛው እምነት ከመጣላችሁ በኋላ እኛ ከለከልናችሁን? አይደለም:: እናንተው ከሓዲያን ነበራችሁ።» ይሏቸዋል። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 34

وَقَالَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُواْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ بَلۡ مَكۡرُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ إِذۡ تَأۡمُرُونَنَآ أَن نَّكۡفُرَ بِٱللَّهِ وَنَجۡعَلَ لَهُۥٓ أَندَادٗاۚ وَأَسَرُّواْ ٱلنَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَۚ وَجَعَلۡنَا ٱلۡأَغۡلَٰلَ فِيٓ أَعۡنَاقِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۖ هَلۡ يُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

33. እነዚያም የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «አይደለም። በአላህ እንድንክድና ለእርሱ ባላንጣዎችን እንድናደርግ ስታዙን (የከለከለን) የሌሊትና የቀን ዱለታችሁ ነው።» ይላሉ:: ቅጣትንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይደብቃሉ:: በእነዚያም በካዱት አንገቶች ላይ እንዛዝሎችን እናደርጋለን:: ይሰሩት የነበሩትን እንጂ ሌላን ይመነዳሉን? info
التفاسير:

external-link copy
34 : 34

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا فِي قَرۡيَةٖ مِّن نَّذِيرٍ إِلَّا قَالَ مُتۡرَفُوهَآ إِنَّا بِمَآ أُرۡسِلۡتُم بِهِۦ كَٰفِرُونَ

34. በየትኛዋም ከተማ አስፈራሪን አላክንም ነዋሪዎችዋ «እኛ በተላካችሁት ከሓዲያን ነን።» ያሉ ቢሆኑ እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 34

وَقَالُواْ نَحۡنُ أَكۡثَرُ أَمۡوَٰلٗا وَأَوۡلَٰدٗا وَمَا نَحۡنُ بِمُعَذَّبِينَ

35. «እኛም በገንዘቦችና በልጆች ይበልጥ የበዛን ነን:: እኛም የምንቀጣ አይደለንም» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 34

قُلۡ إِنَّ رَبِّي يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ

36. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ለሚሻው ሰው ሁሉ ያሰፋል:: ለሚሻው ሰዉም ሁሉ ያጠባል:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህን አያውቁም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 34

وَمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُكُم بِٱلَّتِي تُقَرِّبُكُمۡ عِندَنَا زُلۡفَىٰٓ إِلَّا مَنۡ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَأُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ جَزَآءُ ٱلضِّعۡفِ بِمَا عَمِلُواْ وَهُمۡ فِي ٱلۡغُرُفَٰتِ ءَامِنُونَ

37. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ያች እኛ ዘንድ መቅረብን የምታቀርባችሁ አይደለችም:: ያ በትክክል ያመነና መልካምን የሰራ ብቻ ሲቀር:: እነዚያ ለእነርሱ በሰሩት መልካም ስራ እጥፍ ምንዳ አለላቸው:: እነርሱም በገነት ሰገነቶች ውስጥ ጸጥተኞች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 34

وَٱلَّذِينَ يَسۡعَوۡنَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا مُعَٰجِزِينَ أُوْلَٰٓئِكَ فِي ٱلۡعَذَابِ مُحۡضَرُونَ

38. እነዚያም የሚያቅቱ መስሏቸው አናቅጻችንን ለማበላሸት የሚጥሩ ሁሉ እነዚያ በቅጣት ውስጥ የሚጣዱ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 34

قُلۡ إِنَّ رَبِّي يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦ وَيَقۡدِرُ لَهُۥۚ وَمَآ أَنفَقۡتُم مِّن شَيۡءٖ فَهُوَ يُخۡلِفُهُۥۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ

39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል:: ለእርሱም ያጠባል:: ከማንኛዉም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል:: እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።» በላቸው። info
التفاسير: