Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

ኣሊ-ኢምራን

external-link copy
1 : 3

الٓمٓ

1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 3

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡحَيُّ ٱلۡقَيُّومُ

2. አላህ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ህያው፤ በራሱ የተብቃቃና የሁሉ ነገር አስተናባሪ (የፍጡራን ተንከባካቢ) ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 3

نَزَّلَ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَ

3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ቁርኣንን ከእርሱ በፊት ያሉትን መጽሐፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደው። ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 3

مِن قَبۡلُ هُدٗى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ ٱلۡفُرۡقَانَۗ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٞ ذُو ٱنتِقَامٍ

4. ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል። (በእውነትና በውሸት መካከል መለያ የሆነውን) ፉርቃንንም አወረደ። እነዚያ በአላህ አናቅጽ የካዱ ሁሉ ብርቱ ቅጣት አለባቸው። አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ አስተባባዮችን ተበቃይም ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 3

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَخۡفَىٰ عَلَيۡهِ شَيۡءٞ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِ

5. አላህ በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም ነገር አይሸሸግበትም። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 3

هُوَ ٱلَّذِي يُصَوِّرُكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡحَامِ كَيۡفَ يَشَآءُۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

6. በማህጸኖች ውስጥ እንደፈለገው አድርጎ የሚቀርፃችሁ እርሱው ነው። ከእርሱ ከአሸናፊዉና ከጥበበኛው ጌታ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ በፍጹም የለም። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 3

هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ مِنۡهُ ءَايَٰتٞ مُّحۡكَمَٰتٌ هُنَّ أُمُّ ٱلۡكِتَٰبِ وَأُخَرُ مُتَشَٰبِهَٰتٞۖ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمۡ زَيۡغٞ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَٰبَهَ مِنۡهُ ٱبۡتِغَآءَ ٱلۡفِتۡنَةِ وَٱبۡتِغَآءَ تَأۡوِيلِهِۦۖ وَمَا يَعۡلَمُ تَأۡوِيلَهُۥٓ إِلَّا ٱللَّهُۗ وَٱلرَّٰسِخُونَ فِي ٱلۡعِلۡمِ يَقُولُونَ ءَامَنَّا بِهِۦ كُلّٞ مِّنۡ عِندِ رَبِّنَاۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያ ባንተ ላይ መጽሐፍን-(ቁርኣንን) ያወረደ ነው:: ከመጽሐፉም ውስጥ ግልጽ የሆኑ አናቅጽ አሉ:: እነርሱም የመጽሐፉ መሰረቶች ናቸው። ሌሎች ደግሞ አሻሚ ትርጉም ያላቸው አሉ:: እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሌሎችን ለማሳሳት በማሰብና ትርጉሙን በሻቸው ለመለወጥ ሲሉ አሻሚ ትርጉም (ተመሳሳይነት) ያሏቸውን አናቅጽ ብቻ ይከታተላሉ። ትክክለኛ ትርጉማቸውን አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አያውቀዉም:: እነዚያ በእውቀት የጠለቁት ግን «በእርሱ አምነናል። ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው።» ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶች እንጂ አይገሰጽም። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 3

رَبَّنَا لَا تُزِغۡ قُلُوبَنَا بَعۡدَ إِذۡ هَدَيۡتَنَا وَهَبۡ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحۡمَةًۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡوَهَّابُ

8. (እነርሱም የሚሉ ናቸው:) «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን ወደ መጥፎ አታዘንብልብን:: ካንተ ዘንድ የሆነን ችሮታ ስጠን:: አንተ በጣም ለጋስ ነህና። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 3

رَبَّنَآ إِنَّكَ جَامِعُ ٱلنَّاسِ لِيَوۡمٖ لَّا رَيۡبَ فِيهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُخۡلِفُ ٱلۡمِيعَادَ

9. «ጌታችን ሆይ! አንተ በዚያ ለመምጣቱ ጥርጥር በሌለበት ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ:: ምን ጊዜም አላህ ቀጠሮን አያፈርስምና»:: info
التفاسير: