Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

Broj stranice:close

external-link copy
146 : 2

ٱلَّذِينَ ءَاتَيۡنَٰهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ يَعۡرِفُونَهُۥ كَمَا يَعۡرِفُونَ أَبۡنَآءَهُمۡۖ وَإِنَّ فَرِيقٗا مِّنۡهُمۡ لَيَكۡتُمُونَ ٱلۡحَقَّ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ

146. እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ሰዎች ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ሁሉ (ሙሐመድን) ያውቁታል:: ከእነርሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
147 : 2

ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ

147. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው:: እናም ከተጠራጣሪዎችም አትሁን:: info
التفاسير:

external-link copy
148 : 2

وَلِكُلّٖ وِجۡهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَاۖ فَٱسۡتَبِقُواْ ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ أَيۡنَ مَا تَكُونُواْ يَأۡتِ بِكُمُ ٱللَّهُ جَمِيعًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

148. ለሁሉም ለስግደት ፊታቸዉን የሚያዞሩባት አቅጣጫ አላቸው:: ወደ መልካም ስራዎችም ተሽቀዳደሙ:: የትም ስፍራ ብትሆኑ አላህ ሁላችሁንም ያመጣችኋል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
149 : 2

وَمِنۡ حَيۡثُ خَرَجۡتَ فَوَلِّ وَجۡهَكَ شَطۡرَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۖ وَإِنَّهُۥ لَلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ

149. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ሁነህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አቅጣጫ አዙር:: እርሱም ከጌታህ የሆነ እርግጠኛ እውነት ነው:: አላህም ከምትሰሩት ስራ ሁሉ ዘንጊ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
150 : 2

وَمِنۡ حَيۡثُ خَرَجۡتَ فَوَلِّ وَجۡهَكَ شَطۡرَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۚ وَحَيۡثُ مَا كُنتُمۡ فَوَلُّواْ وُجُوهَكُمۡ شَطۡرَهُۥ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَيۡكُمۡ حُجَّةٌ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مِنۡهُمۡ فَلَا تَخۡشَوۡهُمۡ وَٱخۡشَوۡنِي وَلِأُتِمَّ نِعۡمَتِي عَلَيۡكُمۡ وَلَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ

150.ከየትም ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከለለው መስጊድ አግጣጫ አዙር፡፡ በየትም ስፍራ ብትኾኑ ለሰዎቹ እነዚያ ከነሱ የበደሉት ሲቀሩ (ሃይማኖታችንን ይክዳሉ ቂብላችንን ይከተላሉ በማለት) በናንተ ላይ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው ፊቶቻችሁን ወደ አግጣጫው አዙሩ፡፡ አትፍሩዋቸውም፤ ፍሩኝም፤ (በዚህም ያዘዝኳችሁ መከራከሪያ እንዳይኖራቸው) በናንተም ላይ ጸጋየን እንድሞላላችሁና (ወደ እውነትም) እንድትመሩ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
151 : 2

كَمَآ أَرۡسَلۡنَا فِيكُمۡ رَسُولٗا مِّنكُمۡ يَتۡلُواْ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِنَا وَيُزَكِّيكُمۡ وَيُعَلِّمُكُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمۡ تَكُونُواْ تَعۡلَمُونَ

151. ከመካከላችሁ ከናንተ የሆነን በእናንተ ላይ አናቅጻችንን የሚያነብላችሁ እና የሚያጠራችሁ መጽሐፉንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁን መልእክተኛ እንደላክን ሁሉ ጸጋን ሞላንላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
152 : 2

فَٱذۡكُرُونِيٓ أَذۡكُرۡكُمۡ وَٱشۡكُرُواْ لِي وَلَا تَكۡفُرُونِ

152. አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁና:: አመስግኑኝ አትካዱኝም:: info
التفاسير:

external-link copy
153 : 2

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱسۡتَعِينُواْ بِٱلصَّبۡرِ وَٱلصَّلَوٰةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ

153. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ታጋዙ (ጥንካሬን ፈልጉ):: አላህም ከታጋሾች ጋር ነውና:: info
التفاسير: