Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

Broj stranice:close

external-link copy
27 : 16

ثُمَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يُخۡزِيهِمۡ وَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تُشَٰٓقُّونَ فِيهِمۡۚ قَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ إِنَّ ٱلۡخِزۡيَ ٱلۡيَوۡمَ وَٱلسُّوٓءَ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ

27. ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል:: «እነዚያም በእነርሱ ጉዳይ ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» ይላቸዋል። እነዚያ እውቀትን የተሰጡት ክፍሎች «ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በከሓዲያን ላይ ነው።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 16

ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ ظَالِمِيٓ أَنفُسِهِمۡۖ فَأَلۡقَوُاْ ٱلسَّلَمَ مَا كُنَّا نَعۡمَلُ مِن سُوٓءِۭۚ بَلَىٰٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

28. እነዚያ ነፍሶቻችውን በዳይ ሆነው መላዕክት የሚገድሏቸው «ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርንም» ሲሉ ታዛዥነታቸውን ይገልፃሉ:: «በእውነት አላህ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር አዋቂ ነው።» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 16

فَٱدۡخُلُوٓاْ أَبۡوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ فَلَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلۡمُتَكَبِّرِينَ

29. «የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» ይባላሉ:: የኩሩ ሰዎች ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም በእርግጥ ከፋች! info
التفاسير:

external-link copy
30 : 16

۞ وَقِيلَ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ مَاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمۡۚ قَالُواْ خَيۡرٗاۗ لِّلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٞۚ وَلَدَارُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٞۚ وَلَنِعۡمَ دَارُ ٱلۡمُتَّقِينَ

30. ለእነዚያም ለተጠነቀቁት ሰዎች «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ?» ተባሉ:: «መልካምን ነገር አወረደ» አሉ:: ለእነዚያ ደግ ለሠሩት ህዝቦች ሁሉ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አለላቸው:: የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት:: የጥንቁቆቹም አገር ገነት ምን ታምር! info
التفاسير:

external-link copy
31 : 16

جَنَّٰتُ عَدۡنٖ يَدۡخُلُونَهَا تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ لَهُمۡ فِيهَا مَا يَشَآءُونَۚ كَذَٰلِكَ يَجۡزِي ٱللَّهُ ٱلۡمُتَّقِينَ

31. እርሷም የሚገቧትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትሆን የመኖሪያ አትክልቶች (ጀነት) ናት:: ለእነርሱም በውስጧ የሚሹት ነገር ሁሉ አለላቸው:: ልክ እንደዚሁም አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 16

ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ طَيِّبِينَ يَقُولُونَ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمُ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

32. እነዚያ ጥሩ ሆነው መላዕክት «ሰላም ለእናንተ ይሁን" እያሉ የሚገድሏቸው "ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ምክንያትም ወደ ገነት ግቡ።» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 16

هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ يَأۡتِيَ أَمۡرُ رَبِّكَۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ وَمَا ظَلَمَهُمُ ٱللَّهُ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

33. ከሓዲያን የመላዕክትን ወደ እነርሱ መምጣት ወይም የጌታህ ትዕዛዝ መምጣቱን እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚህ ሠርተዋል:: አላህም አልበደላቸዉም:: ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 16

فَأَصَابَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

34. እናም የሠሯቸዉም ኃጢአቶች ቅጣት አገኛቸው:: ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይ ወረደባቸው:: info
التفاسير: