Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

አት ተካሱር

external-link copy
1 : 102

أَلۡهَىٰكُمُ ٱلتَّكَاثُرُ

1. (በዚህች ዓለም ጸጋዎች) ብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘናጋችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 102

حَتَّىٰ زُرۡتُمُ ٱلۡمَقَابِرَ

2. መቃብሮችን እስከጎበኛችሁ ድረስ:: (በዚሁ ላይ ቀጠላችሁ)። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 102

كَلَّا سَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

3. ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ (ታቀቡ):: ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፤ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 102

ثُمَّ كَلَّا سَوۡفَ تَعۡلَمُونَ

4. ከዚያም ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ። ወደ ፊትም ታውቃላችሁ፤ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 102

كَلَّا لَوۡ تَعۡلَمُونَ عِلۡمَ ٱلۡيَقِينِ

5. በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) በእርግጠኝነት ብታውቁ ኖሮ (ይህን ያክል ባልተዘናጋችሁ ነበር)። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 102

لَتَرَوُنَّ ٱلۡجَحِيمَ

6. ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 102

ثُمَّ لَتَرَوُنَّهَا عَيۡنَ ٱلۡيَقِينِ

7. ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፤ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 102

ثُمَّ لَتُسۡـَٔلُنَّ يَوۡمَئِذٍ عَنِ ٱلنَّعِيمِ

8. ከዚያም በድሎታችሁ ጉዳይ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃለችሁ:: info
التفاسير: