Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Afrička akademija

Broj stranice:close

external-link copy
62 : 10

أَلَآ إِنَّ أَوۡلِيَآءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

62. አስተውሉ! የአላህ ወዳጆች ፍርሀት የለባቸዉም። አይተክዙምም። info
التفاسير:

external-link copy
63 : 10

ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ

63. እነርሱም እነዚያ ያመኑትና አላህን የሚፈሩት ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 10

لَهُمُ ٱلۡبُشۡرَىٰ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۚ لَا تَبۡدِيلَ لِكَلِمَٰتِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

64. ለእነርሱ በቅርቢቱ ህይወትም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብስራት አለላቸው:: የአላህ ቃል አይለወጥም:: ይህ እርሱ ታላቅ እድል (ስኬታማነት) ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 10

وَلَا يَحۡزُنكَ قَوۡلُهُمۡۘ إِنَّ ٱلۡعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًاۚ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግግራቸዉም አያሳዝንህ:: ኃይል በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና:: እርሱም ሰሚውና ሁሉን አዋቂው ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 10

أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَمَا يَتَّبِعُ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُرَكَآءَۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ

66. አስተውሉ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ? ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
67 : 10

هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبۡصِرًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَسۡمَعُونَ

67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ በእርግጥ ብዙ ተአምራት አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 10

قَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدٗاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۖ هُوَ ٱلۡغَنِيُّۖ لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ إِنۡ عِندَكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭ بِهَٰذَآۚ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ

68. «አላህ ልጅን ወለደ።» አሉ። ከሚሉት ሁሉ ጥራት ተገባው:: እርሱ በራሱ ተብቃቂ ነው:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: እናንተ ዘንድ በዚህ በምትሉት ምንም አስረጂ የላችሁም:: በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
69 : 10

قُلۡ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ لَا يُفۡلِحُونَ

69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ሰዎች ፈጽሞ አይድኑም።» በላቸው info
التفاسير:

external-link copy
70 : 10

مَتَٰعٞ فِي ٱلدُّنۡيَا ثُمَّ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ ثُمَّ نُذِيقُهُمُ ٱلۡعَذَابَ ٱلشَّدِيدَ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ

70. እነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ጥቂት ጊዜ ይጠቀሙና ከዚያም መመለሻቸው ወደ እኛ ነው:: ከዚያም ይክዱ በነበሩበት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን:: info
التفاسير: