Prijevod značenja časnog Kur'ana - Prijevod na amharski jezik - Muhammed Sadik

Broj stranice:close

external-link copy
9 : 6

وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ مَلَكٗا لَّجَعَلۡنَٰهُ رَجُلٗا وَلَلَبَسۡنَا عَلَيۡهِم مَّا يَلۡبِسُونَ

(መልክተኛውን) መልአክም ባደረግነው ኖሮ ወንድ ሰው ባደረግነው ነበር፡፡ በእነርሱም ላይ የሚያመሳስሉትን ነገር ባመሳሰልንባቸው ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 6

وَلَقَدِ ٱسۡتُهۡزِئَ بِرُسُلٖ مِّن قَبۡلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُواْ مِنۡهُم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

ካንተ በፊትም በመልክተኞች በእርግጥ ተላግጧል፡፡ በእነዚያም ከእነሱ ባላገጡት ላይ በእርሱ ያላግጡ የነበሩት ነገር (ቅጣት) ወረደባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 6

قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ ثُمَّ ٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ

«በምድር ላይ ኺዱ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 6

قُل لِّمَن مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قُل لِّلَّهِۚ كَتَبَ عَلَىٰ نَفۡسِهِ ٱلرَّحۡمَةَۚ لَيَجۡمَعَنَّكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِۚ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «የአላህ ነው» በል፡፡ «በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ በትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ እነርሱም አያምኑም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 6

۞ وَلَهُۥ مَا سَكَنَ فِي ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

በሌሊትና በቀንም ጸጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂ ነው፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
14 : 6

قُلۡ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيّٗا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَهُوَ يُطۡعِمُ وَلَا يُطۡعَمُۗ قُلۡ إِنِّيٓ أُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ أَوَّلَ مَنۡ أَسۡلَمَۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብ ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ የሰለማ (ትእዛዝን ከተቀበለ) ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 6

قُلۡ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

«እኔ በጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 6

مَّن يُصۡرَفۡ عَنۡهُ يَوۡمَئِذٖ فَقَدۡ رَحِمَهُۥۚ وَذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡمُبِينُ

በዚያ ቀን ከእርሱ ላይ (ቅጣት) የሚመለስለት ሰው (አላህ) በእርግጥ አዘነለት፡፡ ይህም ግልጽ ማግኘት ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 6

وَإِن يَمۡسَسۡكَ ٱللَّهُ بِضُرّٖ فَلَا كَاشِفَ لَهُۥٓ إِلَّا هُوَۖ وَإِن يَمۡسَسۡكَ بِخَيۡرٖ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 6

وَهُوَ ٱلۡقَاهِرُ فَوۡقَ عِبَادِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡخَبِيرُ

እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን አሸናፊ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡ info
التفاسير: