ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا

سورة المزمل - አል ሙዘሚል

external-link copy
1 : 73

يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمُزَّمِّلُ

1. አንተ ተከናናቢው ሆይ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 73

قُمِ ٱلَّيۡلَ إِلَّا قَلِيلٗا

2. ሌሊቱን (ሁሉ) ጥቂት ሲቀር ቁም (ስገድ):: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 73

نِّصۡفَهُۥٓ أَوِ ٱنقُصۡ مِنۡهُ قَلِيلًا

3. ግማሹን (ቁም) ወይም ከእርሱ ጥቂትን ቀንስ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 73

أَوۡ زِدۡ عَلَيۡهِ وَرَتِّلِ ٱلۡقُرۡءَانَ تَرۡتِيلًا

4. ወይም በእርሱ ላይ ጨምር:: ቁርኣንንም በዝግታ አንብብ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 73

إِنَّا سَنُلۡقِي عَلَيۡكَ قَوۡلٗا ثَقِيلًا

5. እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እናወርዳለንና:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 73

إِنَّ نَاشِئَةَ ٱلَّيۡلِ هِيَ أَشَدُّ وَطۡـٔٗا وَأَقۡوَمُ قِيلًا

6. ሌሊት መነሳት (ህዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ነው:: ለማንበብም ትክክለኛ ሰዓት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 73

إِنَّ لَكَ فِي ٱلنَّهَارِ سَبۡحٗا طَوِيلٗا

7. ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም የመዘዋወርያ ሰዓት አለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 73

وَٱذۡكُرِ ٱسۡمَ رَبِّكَ وَتَبَتَّلۡ إِلَيۡهِ تَبۡتِيلٗا

8. የጌታህን ስም አውሳ:: ወደ እርሱም (አምልኮ) መቋረጥን ተቋረጥ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 73

رَّبُّ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَٱتَّخِذۡهُ وَكِيلٗا

9. (እርሱም) የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: መጠጊያ አድርገህም ያዘው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 73

وَٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱهۡجُرۡهُمۡ هَجۡرٗا جَمِيلٗا

10. (ከሓዲያንም) በሚሉት ላይ ታገስ:: መልካምንም መተው ተዋቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 73

وَذَرۡنِي وَٱلۡمُكَذِّبِينَ أُوْلِي ٱلنَّعۡمَةِ وَمَهِّلۡهُمۡ قَلِيلًا

11. የድሎት ባለቤቶችም ከሆኑት አስተባባዮች ጋር ተወኝ:: ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 73

إِنَّ لَدَيۡنَآ أَنكَالٗا وَجَحِيمٗا

12. ከእኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎችና እሳት አሉንና:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 73

وَطَعَامٗا ذَا غُصَّةٖ وَعَذَابًا أَلِيمٗا

13. (ጉሮሮን) የሚያንቅ ምግብና አሳማሚ ቅጣትም አለ። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 73

يَوۡمَ تَرۡجُفُ ٱلۡأَرۡضُ وَٱلۡجِبَالُ وَكَانَتِ ٱلۡجِبَالُ كَثِيبٗا مَّهِيلًا

14. በዚያ ምድርና ጋራዎች በሚርገፈገፉበት፤ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚሆኑበት ቀን:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 73

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡكُمۡ رَسُولٗا شَٰهِدًا عَلَيۡكُمۡ كَمَآ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ رَسُولٗا

15. እኛ ወደ ፊርዖን መልዕክተኛን እንደላክን ሁሉ በእናንተ ላይ መስካሪ መልዕክተኛንም ወደ እናንተ ላክን። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 73

فَعَصَىٰ فِرۡعَوۡنُ ٱلرَّسُولَ فَأَخَذۡنَٰهُ أَخۡذٗا وَبِيلٗا

16. ፊርዓውንም መልዕክተኛውን አመጸ:: ብርቱ መያዝንም ያዝነው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 73

فَكَيۡفَ تَتَّقُونَ إِن كَفَرۡتُمۡ يَوۡمٗا يَجۡعَلُ ٱلۡوِلۡدَٰنَ شِيبًا

17. (በአላህ) ከካዳችሁ ያን ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን ቅጣት እንዴት ትጠነቀቃላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
18 : 73

ٱلسَّمَآءُ مُنفَطِرُۢ بِهِۦۚ كَانَ وَعۡدُهُۥ مَفۡعُولًا

18. ሰማዩ በቀኑ ተሰንጣቂ ነው:: ቀጠሮዉም ተፈፃሚ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 73

إِنَّ هَٰذِهِۦ تَذۡكِرَةٞۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ سَبِيلًا

19. ይህች መገሰጫ ናት። መዳንንም የሻ (የፈለገ) ሰው ወደ ጌታው (የሚያደርሰዉን) መንገድ ይይዛል:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 73

۞ إِنَّ رَبَّكَ يَعۡلَمُ أَنَّكَ تَقُومُ أَدۡنَىٰ مِن ثُلُثَيِ ٱلَّيۡلِ وَنِصۡفَهُۥ وَثُلُثَهُۥ وَطَآئِفَةٞ مِّنَ ٱلَّذِينَ مَعَكَۚ وَٱللَّهُ يُقَدِّرُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَۚ عَلِمَ أَن لَّن تُحۡصُوهُ فَتَابَ عَلَيۡكُمۡۖ فَٱقۡرَءُواْ مَا تَيَسَّرَ مِنَ ٱلۡقُرۡءَانِۚ عَلِمَ أَن سَيَكُونُ مِنكُم مَّرۡضَىٰ وَءَاخَرُونَ يَضۡرِبُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ يَبۡتَغُونَ مِن فَضۡلِ ٱللَّهِ وَءَاخَرُونَ يُقَٰتِلُونَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۖ فَٱقۡرَءُواْ مَا تَيَسَّرَ مِنۡهُۚ وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُواْ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَقۡرِضُواْ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗاۚ وَمَا تُقَدِّمُواْ لِأَنفُسِكُم مِّنۡ خَيۡرٖ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيۡرٗا وَأَعۡظَمَ أَجۡرٗاۚ وَٱسۡتَغۡفِرُواْ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمُۢ

20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን፤ ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መሆንህን ጌታህ ያውቃል:: (ሙስሊሞች) ከእነዚያም አብረውህ ካሉ ከፊሎች የሚቆሙ መሆናቸውንም ያውቃል:: አላህ ሌሊትና ቀንን ይለካል:: ሌሊቱን በሙሉ የማትቆሙት መሆናችሁን አወቀ:: እናም በእናንተ ላይ ህጉን ወደ ማቃለል ተመለሰላችሁ:: ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን ያህል አንብቡ:: ከናንተ ውስጥ ሌሎችም በሽተኞች ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ ሌሎችም፤ በአላህ መንገድ ሃይማኖት ላይ የሚጋደሉ እንደሚኖሩ አወቀ:: አቃለለላቸዉም ከቁርኣን የቻላችሁትን አንብቡ:: ሶላትንም ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: ለአላህ መልካም ብድርንም አበድሩ:: ከመልካም ስራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ:: አላህን ምህረት ለምኑት:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير: