وَإِذَا لَمۡ تَأۡتِهِم بِـَٔايَةٖ قَالُواْ لَوۡلَا ٱجۡتَبَيۡتَهَاۚ قُلۡ إِنَّمَآ أَتَّبِعُ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّ مِن رَّبِّيۚ هَٰذَا بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمۡ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٞ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ
203. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዓምርም ባላመጣህላቸው ጊዜ «በራስህ ለምን አትመርጣትም።» ይላሉ:: «ከጌታዬ ወደ እኔ የተወረደውን ብቻ ነው የምከተለው:: ይህ ቁርኣን ከጌታችሁ የተወረደ ሲሆን ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ መረጃ፤ መመሪያና እዝነት ነው።» በላቸው::
التفاسير: