وَلَقَدۡ صَدَقَكُمُ ٱللَّهُ وَعۡدَهُۥٓ إِذۡ تَحُسُّونَهُم بِإِذۡنِهِۦۖ حَتَّىٰٓ إِذَا فَشِلۡتُمۡ وَتَنَٰزَعۡتُمۡ فِي ٱلۡأَمۡرِ وَعَصَيۡتُم مِّنۢ بَعۡدِ مَآ أَرَىٰكُم مَّا تُحِبُّونَۚ مِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلدُّنۡيَا وَمِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلۡأٓخِرَةَۚ ثُمَّ صَرَفَكُمۡ عَنۡهُمۡ لِيَبۡتَلِيَكُمۡۖ وَلَقَدۡ عَفَا عَنكُمۡۗ وَٱللَّهُ ذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
152. በእርግጥ አላህ በፈቃዱ ጠላቶቻችሁን በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ቃልኪዳንን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ:: የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፣ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመፃችሁም ጊዜ (ግን እርዳታውን ከለከላችሁ):: ከናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከናንተም ውስጥ የመጨርሻይቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ:: በእርግጥም ለእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ:: አላህ ሁልጊዜም በአማኞች ላይ የችሮታ ባለቤት ነውና::
التفاسير: