ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا

رقم الصفحة:close

external-link copy
60 : 23

وَٱلَّذِينَ يُؤۡتُونَ مَآ ءَاتَواْ وَّقُلُوبُهُمۡ وَجِلَةٌ أَنَّهُمۡ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ رَٰجِعُونَ

60. እነዚያም የሚሰጡትን ነገር ሁሉ እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መሆናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ሆነው የሚሰጡ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
61 : 23

أُوْلَٰٓئِكَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَهُمۡ لَهَا سَٰبِقُونَ

61. እነዚያ በመልካም ስራዎች ይጣደፋሉ:: እነርሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
62 : 23

وَلَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ وَلَدَيۡنَا كِتَٰبٞ يَنطِقُ بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ

62. ማንኛይቱንም ነፍስ የችሎታዋን ያህል እንጂ አናስገድዳትም:: እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አለ:: እነርሱም አይበደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 23

بَلۡ قُلُوبُهُمۡ فِي غَمۡرَةٖ مِّنۡ هَٰذَا وَلَهُمۡ أَعۡمَٰلٞ مِّن دُونِ ذَٰلِكَ هُمۡ لَهَا عَٰمِلُونَ

63. በእውነቱ ከሓዲያን ልቦቻቸው ከዚህ መጽሐፍ በዝንጋታ ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱም ከዚህ ሌላ እነርሱ ለእርሷ ሰሪዎችዋ የሆኑ መጥፎ ስራዎች አሏቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 23

حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذۡنَا مُتۡرَفِيهِم بِٱلۡعَذَابِ إِذَا هُمۡ يَجۡـَٔرُونَ

64. ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 23

لَا تَجۡـَٔرُواْ ٱلۡيَوۡمَۖ إِنَّكُم مِّنَّا لَا تُنصَرُونَ

65. (ይባላሉም) «ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱምና። info
التفاسير:

external-link copy
66 : 23

قَدۡ كَانَتۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡ تَنكِصُونَ

66. «አንቀፆቼ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር። እናንተ ግን በተረከዞቻችሁ ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
67 : 23

مُسۡتَكۡبِرِينَ بِهِۦ سَٰمِرٗا تَهۡجُرُونَ

67. «በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ሆናችሁ (ትመለሱ ነበር)።» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
68 : 23

أَفَلَمۡ يَدَّبَّرُواْ ٱلۡقَوۡلَ أَمۡ جَآءَهُم مَّا لَمۡ يَأۡتِ ءَابَآءَهُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ

68. የቁርኣንን ንግግርን አያስተነትኑምን? ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን? info
التفاسير:

external-link copy
69 : 23

أَمۡ لَمۡ يَعۡرِفُواْ رَسُولَهُمۡ فَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ

69. ወይስ መልዕክተኛቸውን አላወቁምን? ስለዚህ እነርሱ በእርሱ ከሓዲያን ናቸውን? info
التفاسير:

external-link copy
70 : 23

أَمۡ يَقُولُونَ بِهِۦ جِنَّةُۢۚ بَلۡ جَآءَهُم بِٱلۡحَقِّ وَأَكۡثَرُهُمۡ لِلۡحَقِّ كَٰرِهُونَ

70. ወይስ «በእርሱ ዕብደት አለበት» ይላሉን? እብድ አይደለም። እውነትን ይዞ መጣላቸው:: አብዛኞቻቸዉም ግን እውነትን ጠይዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
71 : 23

وَلَوِ ٱتَّبَعَ ٱلۡحَقُّ أَهۡوَآءَهُمۡ لَفَسَدَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِذِكۡرِهِمۡ فَهُمۡ عَن ذِكۡرِهِم مُّعۡرِضُونَ

71. እውነታው (አላህ) ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸዉም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር:: ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው:: እነርሱም ክብራቸውን ዘንጊዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
72 : 23

أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ خَرۡجٗا فَخَرَاجُ رَبِّكَ خَيۡرٞۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ

72. ወይስ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግብርን ትጠይቃቸዋለህን? የጌታህም ችሮታ ከሁሉም በላጭ ነው:: እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
73 : 23

وَإِنَّكَ لَتَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

73.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
74 : 23

وَإِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ عَنِ ٱلصِّرَٰطِ لَنَٰكِبُونَ

74. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ግን ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው። info
التفاسير: