قَدۡ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجۡهِكَ فِي ٱلسَّمَآءِۖ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبۡلَةٗ تَرۡضَىٰهَاۚ فَوَلِّ وَجۡهَكَ شَطۡرَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۚ وَحَيۡثُ مَا كُنتُمۡ فَوَلُّواْ وُجُوهَكُمۡ شَطۡرَهُۥۗ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ لَيَعۡلَمُونَ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّهِمۡۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعۡمَلُونَ
144. የፊትህን ወደ ሰማይ ማንጋጠጥክን በእርግጥ ተመልክተናል:: እናም ወደ ምትወዳት (ከዕባ) ቂብላ እናዞርሃለን:: ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙር:: (ሙስሊሞች ሆይ!) የትም ስፍራ ብትሆኑ ስትሰግዱ ፊቶቻችሁን ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙሩ:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: አላህ ከሚሰሩት ስራ ዘንጊ አይደለም፡፡
التفاسير: